በኤሚሬቶች የአቡ ዳቢ የህዋሳት ማበልጸጊያ ማእከል "ADSCC" ተመራማሪዎች አዲስ መድኃኒት ይፋ አድርገዋል
በኤሚሬቶች የአቡ ዳቢ የህዋሳት ማበልጸጊያ ማእከል "ADSCC" ተመራማሪዎች አዲስ መድኃኒት ይፋ አድርገዋል
ለሁለት ሳምንታት ሙከራ የተደረገበትን መድኃኒቱን በተጠቀሙ ግለሰቦች ላይ ምንም አይነት ጉዳት አልታየም ተብሏል፡፡
የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች የጤና ሚኒስቴር በትናንትናው እለት 26,000 የላቦራቶሪ ምርመራ በማድረግ 564 አዲስ የኮሮና ቫይረስ ታማሚዎች መገኘታቸውን ሪፖርት አድርጓል፡፡ በእለቱ 7 ሰዎች ለህልፈት ሲዳረጉ 99 ሰዎች ደግሞ ከቫይረሱ አገግመዋል፡፡ ባጠቃላይ እስካሁን በሀገሪቱ የተገኙ የኮሮና ቫይረስ ታማሚዎች ቁጥር 14,163 ደርሷል፡፡ እስካሁን ለሞት የተዳረጉት ደግሞ 126 ሲሆኑ 2,763 ሰዎች አገግመዋል፡፡