ተ.መ.ድ. “ዘግናኝ” ያለውን የሶማሊያ ጥቀት አወገዘ
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተ.መ.ድ) የጸጥታው ምክር ቤት ለ79 ሰዎች ሞትና ለ149 ሰዎች መጎዳት ምክንት የሆነውን ከትናንት በስትያ በሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ የተከሰተውን ጥቃት በጥብቅ ማውገዙን ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡
የተ.መ.ድ ዋና ጸኃፊ አንቶኒዎ ጉተሬዝ በቃል አቀባያቸው በኩል በወጣው መግላጫ ጥቃቱን ዘግናኝ ነው ያሉት ሲሆን፣ በጥብቅ የሚወገዝ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
ምክርቤቱ ጥልቅ ሀዘኑን ገልጾ ለተጠቂ ቤተሰቦች፣ ለሶማሊያ መንግስትና ህዝብ መጽናናትን ተመኝቷል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ተ.መ.ድ. አጥቂዎችና ጥቃቱን በፋይናንስ በመርዳት አስነዋሪ ተግባር የፈጸሙ አካላት ወደ ህግ የሚቀርቡበትን መንገድ ከሶማሊያ መንግስት ጋር በመሆን ወደ ህግ እንዲቀርቡ እንሰራለን ብሏል፡፡
ዋና ጸኃፊው አንቶኒዎ ጉተሬዝ “የሶማሊያ ህዝብና መንግሰት ለሰላምና ለእድገት የሚያደርገውን ጉዙ“ ተ.መ.ድ በቁርጠኝት ይሰራል ብለዋል፡፡
ምክርቤቱ ሁሉም ሀገራት በአለምአቀፋዊ ሰላምና ጸጥታ ላይ ጉዳት በሚያደርሱ አሸባሪዎች ላይ በሁሉም መንገድ መዋጋት አለባቸው ብሏል፡፡
በሶማሊያ የሚገኙ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ኃላፊም የዋና ጸኃፊውን ሀሳብ በመጋራት ጥቃቱን እንደሚያወግዙ በትዊተር ገጻቸው ጽፈዋል፡፡ አደም አብደልሞውላ የተባሉት እኝህ ኃላፊ ከሶማሊያ ህዝብና መንግሰት ጎን እንደሚቆሙ ገልጸዋል፡፡