የታሰሩት የኳታር ኢሚር ከእስር እንዲፈቱ ሚስታቸው ለተመድ አቤቱታ አቀረቡ
አስማ አሪያ ማመልከቻ ያቀረቡት የኢሚሩ የጤና ሁኔታ እየተባበሰ ከመጣ በኋላ ነው
አሪያንና አሜሪካዊው ጠበቃቸው ማርክ ሶሞስ እንደገለጹት በፖለቲካ ምክንያት የኢሚሩ የፍርድ ሂደት ጉዳይ በትክክል እየታየ አይደለም
አሪያንና አሜሪካዊው ጠበቃዋ ማርክ ሶሞስ እንደገለጹት በፖለቲካ ምክንያት የኢሚሩ የፍርድ ሂደት ጉዳይ በትክክል እየታየ አይደለም
በኳታር የታሰሩት ኢሚር ሸክ ታላል አል ታኒ ሚስት አስማ አሪያን የተባበሩት መንግስታት(ተመድ) የአብአዊ መብት ካውንስል በኳታር ባለስልጣናት ላይ ጫና አድረጎ ባለቤታቸው እንፈቱ እንዲያደርግ አቤቱታ አቅርበዋል፡፡
አስማ አሪያ ማመልቻ ያቀረቡት የኢሚሩ የጤና ሁኔታ እየተባበሰ ከመጣ በኋላ ነው፡፡
አርያን ከፎክስ ኒውሳ ጋር ባደረገችው ቆይታ”ባለቤቴ አስቸኳይ የህክምና እርዳታ ይፈልጋል፤ በደፈናው እስርቤት እያለ የ22 አመት እስራት ተፈርዶበታል፡፡ በነጻነት ለእሱ የሚቆምለትን ጠበቃ መምረጥ ይፈልጋል“ብለዋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ሸክ ታላል አል ታኒ ሰው በማያገኝበት ሁኔታ በመታሰራቸው በከባድ የጤና ችግር ውስጥ እንደሚገኙና የታሰሩበት ቦታ በግልጽ እንደማይታወቅ አሪያን ተናግራለች፡፡ አሪያን እንደተናገሩት ከሆኑ ባቤታቸው ለጤና ችግር የተጋለጡት በእስርቤት በደረሰባቸው ድብደባና ጥሩ ያልሆነ አያያዝ መሆኑን ገልጿች፡፡
አሪያንና አሜሪካዊው ጠበቃቸው ማርክ ሶሞስ እንደገለጹት አሻሚ የሆነው የኳታር የፍርድ ሂደት በፖለቲካ ምክንያት የኢሚሩ ጉዳይ በትክክል እየታየ አይደለም፡፡
ሶሞስ ከሰብአዊ መብት ካውንስል በተጨማሪ በምክንያት የለሽ እስር ዙሪያ ለሚሰራና በእስርቤት ድብደባና ትክክለኛ ባለሆነ ፍርድ ጉዳይ ለሚሰሩትና ለሌሎች የተመድ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች አስቸኳይ አቤቱታ ማቅረባቸውን አስታውቀዋል፡፡
የሽክ ታላል ጉዳይ ዲሞክራሲያዊ ያልሆነችውን ኳታርን ለሌላው አለም ዘመናዊ አድርገው ለማሳየት ለሚጥሩት ለኳታሩ ኢሚር ሸክ ታሚም ቢን ሃማድ አልታኒ እንደመጥፎ አጋጣሚ እየተወሰደባቸው ይገኛል፡፡ የ2022 የአለም እግር ኳስ ዋንጫን የምታስተናግደው ኳታር ሽብርን የማትደግፍ፣ በሰራተኞች የጉልበት ብዝበዛና በሰብአዊ መብት ጥሰት ስሟ የማይጠራ ሀገር እንድትሆን የኳታሩ ኢምር ፍላጎት ነበር፡፡