የአለምጤና ድርጅት የሀገራቱን ክትባት ለማግኘት የሚያስችል እሽቅድምድም ተችቷል
የዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) ሚኒሰትር ናዜም አልዛሃዊ እንዳስታወቁት በአሁኑ ወቅት በመላው አለም 4ሺ የሚሆኑ አዲስ የኮሮና ቫይረስ አይነቶች መኖራቸውንና የኮሮና በሽታ እንደሚያስከትሉ አስታውቀዋል፡፡
ሚኒስትሩ እንዳሉት ፒፋይዘርና አስትራዘኔካን ጨምሮ ሁሉም የክትባት አምራች ድርጅቶች የሚያመርቱትን ክትባት ማሻሻል እንዳለባቸው ገልጸዋል፡፡
በዩኬ ለክትባት ማከፋፈል ሀላፊነት ያለባቸው ሚኒስትሩ ለስካይ ኒውስ እንደተናገሩት የአሁኑ ክትባት በአዲሱ የኮሮና ቫይረስ በተለይም ከባድ ምልክት ባሳዩና በታመሙ ሰዎች ላይ ውጤታማ የማይሆንበት እድል ጠባብ ነው ብለዋል፡፡
ሚኒስትሩ እንደተናገሩት ሁሉም አምራቾች ፒፋይዘር፣ሞደርናና አስትራዜነካ የሚያመርቷቸውን ክትባቶች ለማንኛው አይነት ቫይረስ እንዲሆኑ እያሻሻሉ ነው፤ አራት ሺ የሚሆኑ የሚሆኑ የኮሮና ቫይረሶች አሉ፡፡
የኮሮና ቫይረስ በላፈው አመት ታህሳስ በቻይና ሁቤ ግዛት የተቀሰቀሰ ሲሆን በወራት ውስት መላው አለምን በማዳረስ የማህራዊ፣ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ቀውስን ማስከተል ችሏል፡፡
ሀገራት የኮሮና ቫይረሳ ክትባት ለማግኘት መጠነ ሰፊ ስራ እያከናወኑ ይገኛሉ፤ ግማሾቹም ክትባቱን ማምረት ጀምረዋል፡፡ የአለምጤና ድርጅት የሀገራቱን ክትባት ለማግኘት እሽቅድምድም ተችቷል፤ ቅድሚያ ለድሃ ሀገራት እንዲደርስም አሳስቧል፡፡