ኢኮኖሚ
በታህሳስ 3 የባንኮች የውጭ ምንዛሬ ተመን ዶላር በስንት ብር እየተመነዘረ ነው?
የግል ንግድ ባንኮች ለአንድ ዶላር እስከ 124 ብር እየገዙ ከ124 እስከ 127 ብር እየሸጡ ነው
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ122 ብር ገዝቶ በ125 ብር እየሸጠ ነው
ኢትዮጵያ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርአት ተግባራዊ እንዲደረግ መወሰኗን ተከትሎ ባንኮች በየእለቱ የውጭ ምንዛሬ ተመን ይፋ ማድረጋቸውን ቀጥለዋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ ታህሳስ 3 ቀን 2017 ዓ.ም የውጭ ሀገር ገንዘቦችን የሚገዛበትን እና የሚሸጥበትን ተመን ይፋ ሲያደርግ ከ19 ቀናት በፊት ያወጣውን ዋጋ አስቀጥሏል።
በዚህም አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ122.5986 ብር እየገዛ በ125.0506 ብር እየሸጠ መሆኑን አስታውቋል።
ዳሽን ባንክ እለታዊ የውጭ ምንዛሬ ተመኑን ይፋ ሲያደርግ ህዳር 16 2017 ያወጣውን ተመን ያስቀጠለ ሲሆን አንድ ዶላርን በ124.7171 ብር እየገዛ በ127.2114 ብር እየሸጠ መሆኑን ገልጿል።
ብርሃን ባንክ የምንዛሬ ተመኑ ላይ መጠነኛ የሳንቲም ጭማሪ አድርጓል። በዚህም አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ124.6460 ብር ገዝቶ በ127.1389 ብር እየሸጠ መሆኑን አስታውቋል።
ኦሮሚያ ባንክ ባለፈው ሳምንት ያወጣውን የውጭ ምንዛሬ ተመን አስቀጥሎ አንድ ዶላርን በ124.7099 ብር እየገዛ በ127.2041 ብር እየሸጠ ይገኛል።