በታህሳስ 2 የባንኮች የውጭ ምንዛሬ ተመን የዶላር ዋጋ ስንት ደረሰ?
የግል ንግድ ባንኮች ለአንድ ዶላር ከ122 እስከ 124 ብር መግዣ ከ124 እስከ 127 ብር መሸጫ ዋጋ አቅርበዋል
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ122 ብር ገዝቶ በ125 ብር እየሸጠ ነው
ኢትዮጵያ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርአት ተግባራዊ እንዲደረግ መወሰኗን ተከትሎ ባንኮች በየእለቱ የውጭ ምንዛሬ ተመን ይፋ ማድረጋቸውን ቀጥለዋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ ታህሳስ 2 ቀን 2017 ዓ.ም የውጭ ሀገር ገንዘቦችን የሚገዛበትን እና የሚሸጥበትን ተመን ይፋ ሲያደርግ ከ18 ቀናት በፊት ያወጣውን ዋጋ አስቀጥሏል። በዚህም አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ122.5986 ብር እየገዛ በ125.0506 ብር እየሸጠ መሆኑን አስታውቋል።
ዳሽን ባንክ እለታዊ የውጭ ምንዛሬ ተመኑን ይፋ ሲያደርግ ህዳር 16 2017 ያወጣውን ተመን ያስቀጠለ ሲሆን አንድ ዶላርን በ124.7171 ብር እየገዛ በ127.2114 ብር እየሸጠ መሆኑን ገልጿል።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የትናንቱን የምንዛሬ ተመን አስቀጥሎ አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ124.2066 ብር ገዝቶ በ126.6907 ብር እየሸጠ ነው።
ብርሃን ባንክ የምንዛሬ ተመኑ ላይ መጠነኛ የሳንቲም ጭማሪ አድርጓል። በዚህም አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ124.6456 ብር ገዝቶ በ127.1385 ብር እየሸጠ መሆኑን አስታውቋል።
ኦሮሚያ ባንክ ባለፈው ሳምንት ያወጣውን የውጭ ምንዛሬ ተመን አስቀጥሎ አንድ ዶላርን በ124.7099 ብር እየገዛ በ127.2041 ብር እየሸጠ ይገኛል።