በጥቅምት 9 የባንኮች የውጭ ምንዛሬ ተመን የዶላር ዋጋ ስንት ብር ገባ?
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አንድ ዶላርን በ113 ብር እየገዛ በ115 ብር እየሸጠ ነው
ኦሮሚያ ባንክ አንድ ዶላርን በ121 ብር እየገዛ ሲሆን፤ ሌሎች ባንኮችም መግዣውን ከ115 ብር በላይ አድርሰዋል
ኢትዮጵያ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርአት ተግባራዊ እንዲደረግ መወሰኗን ተከትሎ ባንኮች በየእለቱ የውጭ ምንዛሬ ተመን ይፋ ማድረጋቸውን ቀጥለዋል።
ብሔራዊ ባንክ ከሰሞኑ የውጭ ምንዛሪ መግዣና መሸጫ መሃል ያለው ልዩነት እንዲቀራረብ ባሳሰበ ማግስት የውጭ ምንዛሬ ተመን ላይ ለውጥ ታይቷል።
ባንኮች በውጭ ምንዛሬ መሸጫ ዋጋቸው ላይ ካደረጉት ቅናሽ ባሻገር በመግዣ ዋጋቸውም ላይ ከ10 ብር በላይ ጭማሪ አድርገዋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ ጥቅምት 9 2017 ዓ.ም የውጭ ሀገር ገንዘቦችን የሚገዛበትን እና የሚሸጥበትን ዋጋ ይፋ ሲያደርግ የትናንቱን አስቀጥሏል።
በዚህም አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ113.1308 ብር እየገዛ ሲሆን፤ በ115.3934 ብር እየሸጠ መሆኑን አስታውቋል።
ኦሮሚያ ባንክ ዛሬ ከፍተኛውን የዶላር መግዣ ዋጋ አቅርቧል። ባንኩ ጥቅምት 9 2017 ዓ.ም በእለታዊ የምንዛሬ ተመኑ አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ121.3066 ብር እየገዛ በ123.7327 ብር እየሸጠ መሆኑን ነው በእለታዊ የምንዛሬ ተመኑ ያመላከተው።
አዋሽ ባንክም በዛሬ ጥቅምት 9 2017 የምንዛሬ ዋጋው ከፍ ያለ ዋጋ ያቀረበ ሲሆን፤ ባንኩ በእለታዊ የምንዛሬ ተመኑ አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ119.0155 ብር እየገዛ በ121.3958 ብር እየሸጠ መሆኑን ነው በእለታዊ የምንዛሬ ተመኑ ያመላከተው።
ንብ ባንክ ባወጣው እለታዊ የውጭ ምንዛሬ ተመን መጠነኛ ጭማሪ ያደረገ ሲሆን፤ በዚህም አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ117.1502ብር ገዝቶ በ119.4932 ብር እየሸጠ መሆኑን ይፋ አድርጓል።
ዳሽን ባንክም የጥቅምት 9 2017 የውጭ ምንዛሬ ተመኑን ይፋ ያደረገ ሲሆን፤ የዶላር መግዣ ዋጋው 116.9888 ብር መሆኑን ገልጿል። 119.3286 ብር የባንኩ የዶላር መሸጫ ዋጋ ነው።