ኢኮኖሚ
የጥቅምት 5 የባንኮች የውጭ ምንዛሬ ተመን ምን ይመስላል?
የግል ንግድ ባንኮች 1 ዶላርን እስከ 113 ብር እየገዙ፤ የመሸጫ ዋጋቸውን ዝቅ በማድረግ እስከ 115 ብር እየሸጡ ይገኛሉ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መጠነኛ ጭማሪ በማድረግ 1 ዶላር በ113 ብር እየገዛ፤ መሸጫውን ደግሞ ከ123 ወደ 115 ዝቅ አድርጓል
ኢትዮጵያ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርአት ተግባራዊ እንዲደረግ መወሰኗን ተከትሎ ባንኮች በየእለቱ የውጭ ምንዛሬ ተመን ይፋ ማድረጋቸውን ቀጥለዋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ ጠቅምት 5 2017 ዓ.ም መደበኛ የውጭ ሀገር ገንዘቦችን የሚገዛበትን እና የሚሸጥበትን ዋጋ ይፋ ሲያደርግ ከሰሞኑ ተመን ላይ ማሻሻያዎችን አድርጓል።
በዚህም አንድ የአሜሪካ ዶላርን ከሰሞኑ ሲዛበት ከነበረው በ112.3957 ብር መተኘኛ ጭማሪ በማድረግ በ113.1308 ብር እየገዛ ሲሆን፤ መሸጫውን ዝቅ አድርጎ ከ123 ወደ 115 ዝቅ አድርጓል።
ኦሮሚያ ህብረት ስራ ባክም ባንክም በዛሬው ጥቅምት 5 2017 የውጭ ምንዛሬ ተመኑ 1 የአሜሪካ ዶላርን በ113.0835 ብር እየገዛ ሲሆን፤ መግዣ ዋጋውን በመቀነስ በ115.3452 ብር እየተሸጠ መሆኑን ገልጿል።