ቫይረሱ ከ100 በላይ ሀገራት ተዳርሶ ከ113 ሺ በላይ ሰዎችን ሲያጠቃ ከ 4 ሺ በላይ ገድሏል
በታህሳስ ወር በማእከላዊ ቻይና ከተከሰተ ጀምሮ ኮሮና ቫይረስ በዓለም ተሰራጭቷል፡፡ እስካሁን ቫይረሱ ከ100 በላይ ሀገራት ተዳርሷል፡፡ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከ113,000 በላይ ሰዎች በኮቫይረሱ ተይዘው ከ 4,000 በላይ ሰዎች ሞተዋል፡፡ በኤሲያ (በቻይናና ደቡብ ኮሪያ) አዲስ የሚመዘገቡ የቫይረሱ ተጠቂዎች ቁጥር በከፍተኛ መጠን እየቀነሰ መምጣቱ ተስፋ ሰጪ ቢሆንም በአውሮፓና በአሜሪካ ግን ቁጥሩ እየጨመረ በመሄድ ላይ ነው፡፡