እስካሁን የ45 ሀገራት መሪዎች በአፍሪካ ህብረት ጉባኤ እንደሚሳተፉ አረጋገጡ፡፡
‹‹የጥይት ድምጽ የማይሰማባት፣ ለልማት የምትመች አህጉር እንፍጠር›› የሚል መሪ መልክት አንግቦ የሚካሄደው 33ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ ስኬታማ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ኢትዮጵያ ዝግጅት ማድረጓን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ ለዚህም ባለፉት ሦስት ወራት 33 አባላት ያሉት ብሔራዊ አስተባባሪ ኮሚቴ አቋቁሞ ሲሰራ እንደነበር ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡የ 31 ሃገራት ፕሬዚዳንቶች፣4 ጠቅላይ ሚኒስትሮች፣ የ7 ሃገራት ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች፣ የሦስት ሃገራት ምክትል ፕሬዚዳንቶች የ 14 ሃገራት ቀዳማዊት እመቤቶች በጉባዔው እንደሚሳተፉ አረጋግጠዋለ፡፡