በቻይና የተጠቂዎች ቁጥር ሲቀንስ ከቻይና ውጭ በአንድ ቀን ከ1,400 በላይ ጨምሯል
በቻይና የተጠቂዎች ቁጥር ሲቀንስ ከቻይና ውጭ በአንድ ቀን ከ1,400 በላይ ጨምሯል
ቫይረሱ ስርጭቱን ቀጥሏል፡፡ ብላሩስና ኒው ዝላንድ ትናንት ተጠቂ ሀገራትን ተቀላቅለዋል፡፡ ከቫይረሱ ስጋት ጋር በተያያዘ የዓለም የገበያ እንቅስቃሴ እየቀነሰ መሆኑም ተዘግቧል፡፡ በቻይና የሟቾች ቁጥር ከትናንቱ በ44 ጨምሮ 2,791 ሲደርስ የተጠቂዎች ቁጥር ደግሞ በ359 ጭማሪ አሳይቶ 78,959 ደርሷል፡፡ ከቻይና ውጭ በአንድ ቀን ልዩነት የሟቾች ቁጥር በ15 ከፍ ብሎ 67 ደርሷል፡፡ የቫይረሱ ተጠቂዎች ቁጥር ደግሞ ከ1,400 በላይ ልዩነት አሳይቶ ከ4,400 በላይ ደርሷል፡፡