የእግር እብጠት፣ ስንቆም ማዞር እንዲሁም ጎንበስ የማለት ችግሮች ተጠቃሽ ናቸው
በየአመቱ ኢትዮጵያን ጨምሮ በመላው ዓለም በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን የልብ ህመም እንደሚሞቱ መረጃዎች ያሳያሉ።
የልብ ህመም ከመሰከቱ በፊትም ይሁን ከተከሰተ በኋላ ምልክቶችን የሚያሳይ ሲሆን፤ ነገር ግን አንዳንድ የልብ ጤንነት ዋና ዋና ምልክቶችን ችላ እያልን ሊሆን ይችላል።
የልብ ሐኪም አሚት ባካሂ ችላ ሊሏቸው የማይገቡ 10 ምልክቶችን የዘረዘሩ ሲሆን፤ የእግር እብጠት፣ ስንቆም ማዞር እንዲሁም ጎንበስ የማለት ችግሮች ለምልክቶቹ ተጠቃሽ ናቸው።
ምልክቶቹም፤
1 ከተቀምጥንበት ወይም ከተኛንበት በፍጥነት ስንነሳ የማዞር ችግር
2 ለመተንፈስ መቸገር (ትንፋሽ ቁርጥ ቅርጥ ማለት)
3 ለመጎንበስ (ዝቅ ለማለት መቸገር)
4 የልብ ምት መፍጠን (መጨመር)
5 ደረታችን አካባ የመጨናነቅ (የመጣበብ)
6 የክንድ የአንገት ህመም - አንገት ወይም የላይኛው ክንዶች (ብዙውን ጊዜ በግራ በኩል)
7 ለመቆም መቸገር
8 ደረታችን አካባቢ ምቾት ማጣት
9 የእግር ማበጥ
10 የተዛባ የልብ ምት