በኢራቅ በሰርግ ሰነስርአት ላይ 100 ሰዎች ሲሞቱ፣ ሌሎች 150 ሰዎች ደግሞ ቆሰሉ
በአደጋው የተጎዱ ሰዎችን ህይወት ለማትረፍ አንቡላንሶች እና የህክምና ቡድን አባላት ወደ ቦታው ተልከዋል
በኢራቋ ኒንቬህ ግዛት ውስጥ ከተከሰተው አደጋ የተረፉ ሰዎችን ለመፈለግ የነፍስ አድን ሰራተኞች በአሳት የተገረፈውን ህንጻ በማሰስ ላይ ይገኛሉ
በኢራቅ በሰርግ ሰነስርአት ላይ 100 ሰዎች ሲሞቱ፣ ሌሎች 150 ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል።
በኢራቅ በተካሄደ የሰርግ በተካሄደ የሰርግ ሰነስርአት ላይ ደግሞ በተፈጠረ የእሳት አደጋ 100 ሰዎች የሞቱ ሲሆን 150 ሰዎች የመቁሰል አደጋ እንደደረሰባቸው ሮይተርስ ዘግቧል።
በኢራቋ ኒንቬህ ግዛት ውስጥ ከተከሰተው አደጋ የተረፉ ሰዎችን ለመፈለግ የነፍስ አድን ሰራተኞች በአሳት የተገረፈውን ህንጻ በማሰስ ላይ ይገኛሉ።
የኒንቬህ ግዛት ምክትል አስተዳዳሪ 113 ሰዎች መሞታውን ለሮይተርስ ገልጸዋል። ነገርግን የመንግስት ሚዲያዎች 100 ሰዎች ህይወታቸውን ማጣታቸውን እና 150 ሰዎች መጎዳታቸውን ዘግበዋል።
የአካባቢው የአደጋ መከላከል እንደገለጸው በሰሜን ምስራቅ ግዛት በሚገኘው ትልቅ አዳራሽ ውስጥ እሳት የተነሳው የደስታ ማድመቂያ ርችቶች ከተለኮሱ በኋላ ነው ብሏል።
" እሳቱ ሲንቦገቦግ እና ከአዳራሹ ሲወጣ አየን። መውጣት የቻሉት ወጡ፣ መውጣት ያልቻሉት በእሳቱ ተጠለፉ። የወጡትም የመሰበር አደጋ ደርሶባቸዋል" ሲሉ ኢማድ ዮሃና የተባሉ ከአደጋው ያመለጡ ሰው ተናግረዋል።
በቅድመ ምርመራ የተገኙ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ህንጻውየተሰራው በከፍተኛ ደረጃ ተቀጣጣይ ከሆኑ ቁሶች ነው፤ ይህም ህንጻው በፍጥነት እንዲደረመስ ምክንያት ሆኗል ተብሏል።
በአደጋው የተጎዱ ሰዎችን ህይወት ለማትረፍ አንቡላንሶች እና የህክምና ቡድን አባላት ወደ ቦታው ተልከዋል።