መሪዎቹ ኢኮኖሚውን ለማሻሻል፣ ሙስናን ለመዋጋት እና ስራ አጥነትን ለመታገል የገቡትን ቃል አላሟሉም በሚል ይተቻሉ
ከፈረንጆቹ 2003 የአሜሪካ ወረራ ጀምሮ ኢራቅን ያስተዳደረው ማነው?
በአሜሪካ የሚመራው የኢራቅ ወረራ "ለዳበረ ዲሞክራሲ መንገድ ለመክፈት" ታስቦ ነበር የተካሄደው።
ሆኖም ከፈረንጆቹ 2003 ጀምሮ የተመረጡት መንግስታት በአብዛኛው ውጤታማ ባለመሆናቸው ኢራቃውያንን አሳዝነዋል ተብሏል።
ኢራቃውያን መሪዎቻቸው ኢኮኖሚውን ለማሻሻል፣ ሙስናን ለመዋጋት፣ እየተባባሰ የመጣውን የህዝብ አገልግሎት ለማሻሻል እና ድህነትን እና ስራ አጥነትን ለመታገል የገቡትን ቃል አላሟሉም ይላሉ።
ከሳዳም ሁሴን በኋላ በመጣው አስተዳደር ጠቅላይ ሚንስትሩ አብላጫ ቁጥር ያለው የሺአ ሙስሊም ሲሆኑ፤ አፈ-ጉባኤው ደግሞ ሱኒ ናቸው። የሀገሪቱ ራስ የሆኑት ፕሬዝዳንቱ ቦታ ደግሞ በኩርድ የተያዘ ነው።
ነገር ግን በተለያዩ አጀንዳዎች ምክንያት ከፍተኛ ጫና ውስጥ መውደቅና እና ደም መፋሰስን መከላከል አለመቻሉ ትችት እንዳይለየው አድርጓል።
ሮይተርስ እንደዘገበው ዋናዎቹ የወቅቱ የፖለቲካ ሰዎች የሚከተሉት ናቸው።
አል-ሳድር፤ ሺአዎች፣ሞክታዳ አል-ሳድር እና የሳድሪስት እንቅስቃሴ ፣ ኑሪ አል-ማሊኪ ፣ ሀዲ አል-አሚሪ ፣ቃስ አል-ካዚሊ ፣ኩርዶች እና ሱኒዎች ናቸው።