በግብጽ በቤተክርስቲያን ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ ከ40 በላይ ሰዎች ህይወታቸውን አጡ
ጊዛ ከካይሮ በናይል ወንዝ ማዶ የምትገኝ የግብፅ ሁለተኛዋ ትልቅ ከተማ ነች
እሳት አደጋው የተከሰተው በጊዛ በሚገኘው የአቡ ሲፈን ኮፕቲክ ቤተክርስቲያን ላይ ነው
በግብጽ ጊዛ በተባለ ቦታ በአንድ ቤተክርስቲያን ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ ከ40 በላይ ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡
በግብፅ ጊዛ ከተማ በሚገኝ ቤተክርስትያን ውስጥ በደረሰ የእሳት ቃጠሎ ቢያንስ 40 መሞታቸውን እና 45 መቁሰለቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
በኢምባባ ሰፈር በሚገኘው ኮፕቲክ አቡ ሲፊን ቤተክርስቲያን 5 ሺ ሰዎች በተሰበሰቡበት ወቅት በኤሌክትሪክ ምክንያት እሳት መነሳቱን ሮይተርስ ምንጮችን ተቅሶ ዘግቧል፡፡ የተነሳው እሳት የቤተክርሲያኑን መግቢያ በመዝጋቱ ምክንያት ትርምስ እንዲፈጠር ምክንያት ሆኗል፤ ከሟቾቹ መካከልም አብዛኞቹ ህጻናት መሆናቸውን ዘገባው ጠቅሷል፡፡
“በሦስተኛውና አራተኛው ፎቅ ላይ ሰዎች እየተሰበሰቡ ነበር፣ እና ከሁለተኛው ፎቅ ጭስ ሲወጣ አየን። ሰዎች ደረጃውን ለመውረድ እየተጣደፉ እርስ በእርሳቸው እየተተያዩ ተፋጠጡ” ሲል የቤተክርስቲያኑ አምላኪ ያሲር ሙኒር ተናግሯል።
"ከዚያም ጩኸት እና ብልጭታ እና እሳት በመስኮት ሲወጣ ሰማን" ሲል እሱና ሴት ልጁ መሬት ላይ ሆነው ማምለጥ እንደቻሉ ተናግሯል።
ጊዛ፣ የግብፅ ሁለተኛዋ ትልቅ ከተማ፣ ከካይሮ በናይል ወንዝ ማዶ ትገኛለች።