ትናንት ከተከሰከሰው የኔፓል አውሮፕላን አደጋ የ14 ሰዎች አስከሬን ተገኘ
አውሮፕላኑ በትናንትናው ዕለት 22 ሰዎችን አሳፍሮ ሲበር መሰወሩ ይታወሳል
አውሮፕኑ ለማረፍ አምስት ደቂቃ ሲቀረው ከመቆጣጠሪያ ጣቢያው ያለው ግንኙነት ተቋርጧል
ትናንት ከተከሰከሰው የኔፓል አውሮፕላን አደጋ የ14 ሰዎች አስከሬን ተገኘ።
ንብረትነቱ የግል አየር መንገድ የሆነ አነስተኛ የመንገደኞች አውሮፕላን በትናንትናው ዕለት 22 ሰዎችን አሳፍሮ በመብረር ላይ ሳላ በተራራማዋ የኔፓል ቦታ የደረሰበት መጥፋቱ ይታወሳል።
ባለስልጣናት እንደተናገሩት የአካባቢው ሰዎች እሳት ማየታቸውን ወደገለጹበት ቦታ የፍለጋ ቡድን ማሰማራታቸውን የገለጹ ሲሆን ዛሬ ረፋድ በወጣው የፍለጋ ሪፖርት መሰረት የ14 ሰዎች አስከሬን መገኘቱን ሮይተርስ ዘግቧል።
የቀሪ ተሳፋሪዎችን አስከሬን በመፈለግ ላይ መሆናቸውን የተናገሩት ባለስልጣናቱ ተጨማሪ መረጃዎችን በቀጣይ እንደሚሰጡም አክለዋል።
የኔፓል ቴሌቪዥን በልያንኩ ኮህል አካባቢ ያሉ ሰዎችን ጠቅሶ እንደዘገበው ቲቤትን በሚያዋስነው የሂማሊያ ተራራ ስር አርክራፍቷ በእሳት ስትያያዝ አይተናል ማለታቸው ይታወሳል።
ዲ ሃቪላንድ ካናዳ ዲኤች ሲ-6-300 ጠዊነ ኦተር ለ20 ደቂቃ በራራ የተነሳ ቢሆን ለማረፍ አምስት ደቂቃ ሲቀረው ከመቆጣጠሪያ ጣቢያው ያለው ግንኙነት ተቋርጦ ቁጥጥሩን የሚያደርገው የታራ ኤየር ኩባንያ ነበር።
አራት ህንዳውያን፤ ሁለት ጀርመናውያንን እና 16 የኔፓል ዜጎችን አሳፍሮ ነበር ያለው አየርመንገዱ በረራው ከኔፓል ዋና ከተማ ከታማንዱ ዋና ከተማ በምስራቅ በኩል 125 ኪሜ ርቀት ወደምትገኘው የቱሪስት መዳረሻዋ ፖክሃራ ከተማ ነበር።
በፈረንጆቹ 1992፣167 ሰዎች አሳፈሮ ሲበር የነበረው የፓኪስታን አለምአቀፍ አውሮፕላን ካታማንዱ ለማረፍ ትንሽ ሲቀረው ከተራራ ጋር ተጋጭሮ ሁሉም ተሳፋሪዎች መሞታቸው ይታወሳል።