በተከሰከሰው የቻይና አውሮፕላን ውስጥ የነበሩ ሁሉም ተሳፋሪዎች መሞታቸውን ቻይና ገለፀች
ከተሳፋሪዎች ውስጥ 123 መንገደኞች ሲሆኑ 9 የበረራ ቡድን አባላት ናቸው
የቻይና ኢስተርን አየር መንገድ አውሮፕላን 132 ሰዎችን አሳፍሮ መከስከሱ ይታወሳል
132 ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረው የቻይና ኢስተርን አየር መንገድ የሆነው ቦይንግ 737-800 በሀገር ውስጥ በረራ ላይ ሳለ በደቡባዊ ቻይና ግዛት በሚገኝ ተራራማ አካባቢ መከስከሱ ይታወሳል።
አደጋውን ተከትሎ የነፍስ አድን ስራውን የሚመራው የቻይናው ባለስልጣን፤ በተከሰከሰው MU5735 የመንገደኞች አውሮፕላን ውስጥ የነበሩ 132 ተሳፋሪወች ህይወት ማለፉን አስታውቋል።
አደጋው በደረሰበት አካባቢ የስለላ ካሜራዎች፣ ራዳር እና ሌሎች መሳሪያዎች በመጠቀም የፍለጋ ስራ ሲያከናውን ቆየው ባለስልጣኑ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ “እስከ ትናት ቅዳሜ ድረስ የ120 ማንነት በDNA ምርመራ ማንነታቸውን አረጋግጫለሁ ብሏል።
አውሮፕላኑ የመከስከስ አደጋ የደረሰበት ከዩናን ግዛት ዋና ከተማ ወደ ወደ ጓንግ ዶንግ ዋና ከተማ ወደ ሆነችው ጉዋንዙ በመጓዝ ላይ ሳለ ነበር።
የቻይናው ኢስተርን አየርመንገድ እንደገለጸው አውሮፕላኑ ከ31 ሺህ ጫማ ተምዘግዝጎ እንዲከሰከስ ያደረገው ምክንያት በምርመራ ላይ ነው ተብሏል። ሮይተርስ የቻይናን ሚዲያ ጠቅሶ እንደዘገበው በበራራው ላይ የውጭ ሀገር ዜጋ የለም።
ጉዋንዡ የአውሮፕላን አደጋ ቀደም ብሎ በቦይንግ 737-800 አውሮፕላን ታሪክ 22 አደጋዎች ያጋጠሙ ሲሆን፤ ከኢነዚህም ውስጥ 10 አደጋዎች የበርካቶችን ህይወት የቀጠፉ ናቸው።
ከ22ቱ አደጋዎች ውስጥ የመጀመሪያው የቦይንግ 737-800 አውሮፕላን አደጋ በፈረንጀቹ በ2006 በብራዚል ያጋጠመ ሲሆን፤ በአደጋውም 154 ሰዎች መሞታቸው ይታወሳል።
የቅርቡ የቦይንግ 737-800 አውሮፕላን አደጋ ደግሞ በህንድ ያጋጠመ ሲሆን፤ በአደጋውም 21 ሰዎች መሞታቸው ተነግሯል።