ቀናችንን ቀለል ባለ ቁርስ መጀመርና በእራት ሰዓት ስብ የበዛባቸውን ምግቦች አለመመገብ ይመከራል
1444ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል በዛሬው እለት ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያየ የዓለም ሀገራት በተለያዩ ስነ ስርዓቶች በመከበር ላይ ይገኛል።
ታዲያ 1 ወር ሙሉ በጾም ላይ የከረሙ ሰዎች የበዓል ሰሞን የምግብ አወሳሰዳቸው ጥንቃቄ የተሞላበት ሊሆን እንደሚገባ ጤና ባለሙያዎች ይመክራሉ።
ቁርሳችን ላይ ቀለል ያሉ ምግቦችን መመገብ፣ ምግብ በምንመገብበት ሰዓት በዝግታ እና በደንብ አኝኮ መዋጥ እንዲሁም በበዓል ሰሞን እንደ ቸኮሌት ያሉ ጣፋጭ ነገሮች አወሳደዳችን ላይ መጠንቀቅ አለብን ይላሉ።