ውሃ መጠጣት፣ ከመኝታ በፊት ሙቅ ሻወር መውሰድ እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ከችግሩ የሚገላግሉ ፍቱን መላ ናቸው ተብሏል
በአሜሪካ ከ52 በመቶ በላይ ወጣቶች ሲተኙ እንደሚያንኮራፉ አዲስ ጥናት አሳይቷል።
ዋንፖል በ2 ሺህ ወጣቶች ላይ ያደረገው የዳሰሳ ጥናት የማንኮራፋት ችግር ምን ያህል ስር እየሰደደ መምጣቱን አመላክቷል።
ማንኮራፋት እንቅልፍን በመበጥበጥ 38 በመቶ የሚሆኑ ጥንዶችን አልጋቸውን እንዲለያዩ ማድረጉን ጉድ ኒውስ ኔትወርክ ላይ የወጣው ጥናት አሳይቷል።
60 በመቶ የሚሆኑት የጥናቱ ተሳታፊዎችም ችግሩ እንደማይቀረፍ ወደማመኑ መቃረባቸው ተመላክቷል።
ጥናቱ ከማንኮራፋት ችግር ያወጣሉ ተብለው በተሳታፊዎቹ የተመከሩ ነጥቦችንም እንደሚከተለው ጠቁሟል፤ ይመልከቷቸው፦