ልዩልዩ
ዜጎቻቸው ከማዕዳቸው ስጋ እንዲጠፋ የማይፈልጉ ሀገራት
ስታስቲስታ የተሰኘው ተቋም የዳሰሳ ጥናት አድርጎ ስጋ በብዛት የሚበላባቸውን ሀገራት ይፋ አድርጓል
በጥናቱ 60 ሺህ ሰዎች የተሳተፉ ሲሆን፥ 86 ከመቶው ስጋ እንደሚወዱ ገልጸዋል
ስጋ መመገብ በመላው አለም የተለመደ ባህል ይሁን እንጂ በአንዳንድ ሀገራት ከማዕድ በፍጹም እንዲጠፋ አይፈለግም።
ስታቲስታ የተሰኘው የስታትስቲክስ ተቋም ያደረገው ጥናትም ዜጎቻቸው እጅግ ስጋ የሚወዱና በተለያየ መልኩ ከማዕዳቸው የማይጠፋ ሀገራትን ይፋ አድርጓል።
ተቋሙ በተለያዩ ሀገራት ለ60 ሺህ ሰዎች መጠይቆችን በመበተንና ቃለመጠይቅ በማድረግ አጠናቀርኩት ባለው መረጃ፥ 86 በመቶ የሚሆኑት የጥናቱ ተሳታፊዎች ስጋ ወዳጅ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ስጋ ያጡትም ሆኑ ለጤናችን አይመከርም የሚሉት እንኳን የስጋ ጣዕም ያላቸውንና ስጋን የሚተኩ ነገሮችን እንደሚገዙ ነው ጥናቱ ያመላከተው።
በስታቲስታ ጥናት መሰረት ዜጎቻቸው ከማዕዳቸው ስጋ እንዲጠፋ የማይፈልጉ ናቸው የተባሉትን ሀገራት ይመልከቱ፦