ባለፉት 20 ዓመታት 2 ሽህ የሚጠጉ ጋዜጠኞች ተገድለዋል ተባለ
ድንበር የለሽ የጋዜጠኞች ቡድን ባወጣው ሪፖርተር ከፈረንጆቹ ከ2003 እስከ 2022 ያሉት ሁለት አስርት ዓመታት ለጋዜጠኞች ገዳይ አስርት ዓመታት ነበሩ
ኢራቅ እና ሶሪያ በጋዜጠኝነት ለመስራት በጣም አደገኛ ሀገራት ናቸው ተብለዋል
ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት በዓለም አቀፍ ደረጃ ወደ አንድ ሽህ 700 የሚጠጉ ጋዜጠኞች መገደላቸውን ድንበር የለሽ የጋዜጠኞች ቡድን አስታውቋል።
ይህም በዓመት በአማካይ ከ80 በላይ ጋዜጠኞች ተገድለዋል ማለት ነው።
ድንበር የለሽ የጋዜጠኞች ቡድን ባወጣው ሪፖርተር በፈረንጆቹ ከ2003 እስከ 2022 ባሉት ሁለት አስርት ዓመታት ለመረጃ አሳሾች ገዳይ አስርት ዓመታት ነበሩ ብሏል።
የቡድኑ ዋና ጸሃፊ ክሪስቶፍ ዴሎየር እንዳሉት "ከቁጥሩ ጀርባ መረጃ ለመሰብሰብ፣ እውነትን ፍለጋና ለጋዜጠኝነት ፍቅር ሲሉ ህይወታቸውን የከፈሉ ሰዎች ፊት፣ ስብዕና፣ ተሰጥኦ እና ቁርጠኝነት አለ።
ኢራቅ እና ሶሪያ በጋዜጠኝነት ለመስራት በጣም አደገኛ ሀገራት ናቸው የተባለ ሲሆን፤ ሀገራቱ በድምሩ 578 ጋዜጠኞች ባለፉት 20 ዓመታት ተገድሎባቸዋል።
ይህም ከዓለም አጠቃላይ አንድ ሶስተኛው በላይ ነው ሲል ቡድኑ ገልጿል።
ሜክሲኮ 125 ጋዜጠኞች የገደሉባት ሀገር መሆን በሦስተኛ ደረጃ ትከተላለች።
ፊሊፒንስ (107)፣ ፓኪስታን (93)፣ አፍጋኒስታን (81) እና ሶማሊያ (78) ከፍተኛ ጋዜጠኞች የተገደሉባቸው ሀገራት ናቸው።
"በጣም የጨለማው ዓመታት" ከፈረንጆቹ 2012 እና 2013 ነበሩ።
ሪፖርቱን ጠቅሶ ፍራንስ 24 እንደዘገበው በሶሪያ ጦርነት ምክንያት እ.ኤ.አ. በ2012 144 ግድያዎች፤ ከአንድ ዓመት በኋላ ደግሞ142 ግድያዎች ነበሩ ብሏል።