ሩሲያ ከዚህ በፊት ቢቢሲን ጨምሮ ሌሎች ሚዲያዎች ተደራሽ እንዳይሆኑ ዘግታለች
ሩሲያ የጀርመኑን ዲ ቬልት ጋዜጣ ድረ-ገጽ እንዳይታይ እገዳ የጣለችው በዓቃቤ ህግ ጥያቄ መሠረት መሆኑን
የሀገሪቱ የኮሙኒኬሽን ተቆጣጣሪ አስታወቀ።
የሩሲያ ባለስልጣናት ሞስኮ በዩክሬን ውስጥ እያካሄደች ያለውን እና "ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ" ስትል የሰየመችውን ዘመቻ በተመለከተ የምዕራቡ ዓለም የውሸት መረጃ አሰራጭቷል ሲሉ ይከሳሉ።
በፈረንጆቹ የካቲት 24 ቀን ሩሲያ ወታደሮቿን ወደ ዩክሬን ግዛት ካስገባች በኋላ የቢቢሲ፣ የአሜሪካ ድምፅ፣ የዶይቸ ቬለ እና የሌሎች መገናኛ ብዙሃን ተደራሽ እንዳይሆኑ ዘግታለች።
ሮይተርስ ድረገጹ ለምን እገዳ እንደተጣለበት የሩሲያን የኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ቢጠይቅም መልስ አለመግኘቱን ገልጿል።
ሩሲያ የኔቶ ጦር ወደ ቀድሞ የሶቬት ሀገራት መስፋፋት ለደህንነቷ እንደማያሰጋት በመግለጽ ነበር በዩክሬን ላይ "ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ" ያወጀችው።
ከዚህ በተጨማሪም ዩክሬንን ትጥቅ ማስፈታት እና የናዚን አስተሳሰብ ማጥፋት የዘመቻው አላማ መሆኑን ሩሲያ መግለጿ ይታወሳል።
በሩሲያ ርምጃ የተቆጡት ምእራባውያን ሩሲያን ያዳክማል ያሉትን ሁሉ ማእቀብ በሩሲያ ላይ ጥለዋል።
ጦርነቱ አሁንም በደቡብ እና ምሰራቃዊ ዩክሬን ቀጥሏል።