ኳታር ሄዝቦላን እንደምትደግፍ የሚያመላክት ዶሴ ተገኘ
የአውሮፓ ፖለቲከኞች ኳታር ለሄዝቦላህ ትረዳለች የሚለውን ነገር ለማስቆም ፖሊሲ ያስፈልጋል ብለዋል
የአሜሪካው ሮክስ ኒውስ እንደዘገበው ኳታር የሄዝቦላን ሽብር እንቅስቃሴን ትረዳላች መባሉ የአሜሪካን ወታደሮች ችግር ላይ እንደጣለ ተገለጸ
የአሜሪካው ፎክስ ኒውስ እንደዘገበው ኳታር የሄዝቦላን ሽብር እንቅስቃሴን ትረዳላች መባሉ የአሜሪካን ወታደሮች ችግር ላይ እንደጣለ ተገለጸ
የአሜሪካው የፎክስ ኒውስ አገኘሁት ባለው ዶሴ የኳታር ንጉስ አለምአቀፍ የሽብር ቡድን ለሆነው ሄዝቦላ ቡድን የጦር መሳሪያ ድጋፍ ያደርጋሉ መባሉ ወደ 10ሺ የሚጠጉ የአሜሪካ ወታደሮችን አደጋ ላይ ጥሏል ተብሏል፡፡ የባህረሰላጤዋ አል ኡዳይድ የተባለው የጦር ሰፈር የአሜሪካን የማእከላዊ እዝና አሜሪካ አየር ኃይል መቀመጫ መሆኑ ይታወቃል፡፡
የግል የጸጥታ ኮንትራክተር የሆነው ጃሰን ጂ. የኳታርን መሳሪያ ግዥ ሂደት ውስጥ ጣልቃ በመግባት አደገኛ የሆነ አካሄድ አካል መሆኑ ተጠቅሷል፡፡ ባለፈው ማክሰኞ ለፎክስ ኒውስ እንደተናረው የኳታር የገዥ መደብ በአሜሪካና በአውሮፓ በአሸባሪነት ለተፈረጀው ለሊባኖሱ ሄዝቦላ የመሳሪያ አቅርቦት ፈቅዷል ብሏል፡፡
በጃሰን በሰጠው ዶሴና በፎክስ ኒውስ በተረጋገጠው ከሆነ ዶሴው የኳታር ገዥ መደብ ከፈረንጆቹ 2017 ጀምሮ ሄዝቦላን ለመደገፍ የተጫወተው ሚና እንዳለ ይጠረጥራል፡፡
የሊባኖሱ ሄዝቦላህ ቡድን ለኢራኑ ሺያ ሚሊሺያ ቅርበት እንዳለውና የተመሰረተውም በቴህራን እስላማዊ አብዮታዊ ጠባቂ በፈረንጆቹ 1982 ነው የተመሰረተው፡፡ቡድኑ በኢራቅና በሊባኖስ ለሞቱ በመቶዎች ለሚቆጠሩ ወታደሮች የአሜሪካ ወታደሮች ሃላፊነት ይወስዳል ተብሏል፡፡
በቤልጄምና በኔቶ የኳታር አምባሳደር አብዱራህማን ቢን መሃመድ ሱሌማን አል ከሊፋ ለጃሰን ጂ. 750ሺ ዩሮ በመክፈል ለሌባኖሱ ሻይት ታጣቂ ብርና የጦር መሳሪያ እንዲያቀብል ሲያግባቡ ነበር፡፡
ጃሰን በፈረንጆቹ 2019 ከአምባሳደር ከሊፋ ጋር በብራሰልስ በነበራቸው ቆይታ፤ አምባሳደሩ ጀዊሾች ጠላቶቻችን ናቸው ማለታቸውን ይጠቅሳል፡፡
በጉዳዩ ላይ ኔቶም ሆነ የቤልጀም መንግስት ምላሽ አልሰጡም ብላል ፎክስ ኒውስ፡፡
ጃሰን ጂ ከኳታር በቀል ለማምለጥ ሀሰተኛ ስም ይጠቀም ነበር፤ ነገርግን ጃሰን ሲናገር ይህን ያደርግ የነበረው ኳታር ሽብርተኞችን ከመርዳት እንድትታቀብ በመፈለግ መሆኑን ይናገራል፡፡ እንደ ጃሰን ከሆን የተበላሸ አፕል ከበርሜሉ በማውጣት ኳታርን የአለምአቀፍ ማህበረሰብ አካል ለማድረግ መሆኑን ይናገራል፡፡
በፈረንጆቹ 2017 ዶናልድ ትራምፕ ኳታር የሽብር ቡድን በከፍተኛ መጠን ትደግፋለች ብለው ነበር፡፡ ነገርግን ትራምፕ ከሀገሪቱ ኢሚር ታሚም ቢን ሀማድ አልታኒ ጋር በነበራቸው ቆይታ ኳታር ሽብርተኝነትን እንደምትዋጋ ገልጸውም ነበር፡፡
በቅርብ የተገኘውና ኳታር በአለም ላይ እጅግ አደገኛ የሚባለውን የሽብር ቡድን ትረዳለች መባሏ፤ የገልፍ ባህረሰላጤዋን ሀገር ከአሜሪካ ጋር ያላትን ወታደራዊ ቅርርብ ጥላ አጥልቶበታል ተብሏል፡፡
ታዋቂ የአውሮፓ ፖለቲከኞች ከፎክ ኒውስ ጋር በነበራቸው ቆይታ ኳታር ለሂዝቦላህ ትረዳለች የሚለውን ነገር ማስቆም ፖሊሲ ያስፈልጋል ተብሏል፡፡ የጂሃዲስትን ትስስር ምርመራ የመሩት ናታሊ የተባለው የፈረንሳይ ሴናተር እንዳሉት ኳታር ለሽብርተኞች የምታደርገውን ድጋፍ ለማስቆም ፖሊሰ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ ቤልጀምም የአውሮፓን ህብረት ምርመራ እንዲያደርግ መጠየቅና የኳታርን ባንኮች አካውንት መዝጋት እንዳለባት ተናግሯል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ሴናተሯ እንዳሉት በተለይ አደገኛ የጸረ-ሴሜቲዝምና የሙስሊም ወንድማማቾችን የሚደግፍትን ኳታርና ቱርክን ለማስቆም ጠቅላላ የፖሊሲ ማእቀፍ ማዘጋጀት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም የጀርመንና የእንግሊዝ ፖለቲከኞች ኳታር ሄዝቦላን በገንዘብና በጦርመሳሪያ ትረዳለች የሚባለው ጉዳይ በትኩረት መታየት አለበት የሚል ሀሳብ አስተላልፈዋል፡፡