ደቡብ አፍሪካ 24ሺ የሚሆኑ የጤና ባለሙያዎች አንደተያዙባት አስታወቀች
ደቡብ አፍሪካ 24ሺ የሚሆኑ የጤና ባለሙያዎች አንደተያዙባት አስታወቀች
የደቡብ አፍሪካ የጤና ሚኒስቴር እንዳስታወቀው ባለፈው መጋቢት የኮሮና ቫይረሳ ሀገሪቱን ከመታት በኋላ በትንሹ 24 ሺ የሚሆኑ የጤና ባለሙያወች በኮሮና ቫይረስ ተይዘዋል፡፡
የጤና ሚኒስትር ዘዌል ምክዊዜ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ የጤና ባለሙያዎች ከ24ሺ በላይ መሆናቸውንና ከነዚህም ውስጥ 181 ሰዎች መሞታቸውን አስታውቀዋል፡፡
በኮሮና የተጠቁ የጤና ባለሙያዎች በሀገሪቱ በኮሮና ቫይረስ ከተያዙ ሰዎች ውስጥ አምስት በመቶ አንደሚሸፍኑ አስታውቀዋል፡፡ በሀገሪቱ በኮሮና ቫይረስ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር በፍጥነት እየጨመረ መጥቷል፡
በመጋቢት ወር ተጥሎ የነበረው ጥብቅ ቁጥጥር ከላላ በኃላ የሀገሪቱ የጤና ባለስልጣናት የኮሮና ተጠቂዎች ቁጥር እንደሚጭር ይጠብቁ ነበር፡፡ደቡብ አፍሪካ በአለም በከፍተኛ መጠን ከተጠቁ ሀገራት መካከል በአምስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ፡፡
ደቡብ አፍሪካ በአፍሪካ በከፍተኛ መጠን የተጠቃች ሲሆን ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ሰዎች ተጠቅተዋል፤ይህም በአፍሪካ በቫይረሱ የተያዙትን ከግማሽ በላይ ይሆናሉ፡፡