በስድስት አመቱ የተሰረቀው ህጻን ከ73 አመታት በኋላ በህይወት ተገኘ
ሊዩስ አርማንዶ አልቢኖ ከታላቅ ወንድሙ ሮገር ጋር እየተጫወተ ከነበረበት ፓርክ ነበር በየካቲት 1951 በአንዲት ሴት የተሰረቀው
በ1951 የስድስት አመት ህጻን እያለ የተሰረቀው ህጻን የእህቱ ልጅ ባደረገችው ብርቱ ፍለጋ ከተጠፋፋው ወንድሙ ጋር ሊገናኝ ችሏል
በስድስት አመቱ የተሰረቀው ህጻን ከ73 አመታት በኋላ በህይወት ተገኘ።
በ1951 የስድስት አመት ህጻን እያለ የተሰረቀው ህጻን የእህቱ ልጅ ባደረገችው ብርቱ ፍለጋ ከተጠፋፋው ወንድሙ ጋር ሊገናኝ ችሏል።
አሁን የ79 አመት እድሜ ባለጸጋ የሆነው ሊዩስ አርማንዶ አልቢኖ ከታላቅ ወንድሙ ሮገር ጋር እየተጫወተ ከነበረበት ፓርክ ነበር በየካቲት 1951 በአንዲት ሴት የተሰረቀው።
ዴይሊሜል እንደዘገበው የሰረቀችው ሴት መንጭቃ ከምዕራብ ኦክላንድ ወደ ምስራቅ ጫፍ ከመውሰዷ በፊት ከረሜላ እገዛልሃለሁ የሚል ማታለያ ተጠቅማለች። ከዚህ ጊዜ ጀምሮ የኒው ዮርክ ጥንጆች ሊዩስን እንደራሳቸው ልጅ አሳድገውታል።
ቤተሰቦቹ እንደገለጹት እናቱ በ2005 በአሳዛኝ ሁኔታ የሞቱት እናቱ በሊዩስ ተስፋ ቆርጠው አያቁም ነበር፣ አንድ ቀን ወደ ቤቱ ይመጣል የሚል ተስፋ ነበራቸው።
የሊዩስ የእህት ልጅ የሆነችው አሊዳ አሊቁይን በዲኤንኤ ምርመራ እና በጋዜጣ አጎቷን ስታፈላልግ ቆይታለች። አሁን ኦክላንድ የምትገኘው አሊዳ ሊዩስን ለመፈለግ በምታደርገው ጥረት የአካባቢውን ፖሊስ፣ የአሜሪካን የፌደራል ወንጀል ምርመራ ቢሮ(ኤፍቢአይ) እና የፍትህ ሚኒስቴርን ድጋፍ ጠይቃም ነበር።
አሊዳ ሊዩስን በመፈለግ ወሳኝ ሚና ተጫውታለች ያለው የአከባቢው ፖሊስ አድናቆት ችሯታል። አሊዳ ከ73 አመት በፊት የተለያዩት ወንድማማቾች እንዲገኙ ፕሮግራም አዘጋጅታለች።
ሊዩስ የእህቱን ልጅ አሊዳን አቅፎ "ስለፈለግሽን አመስግናሉ" ብሏታል።
ሊዩስ ባለፉት ሰባት አስርት አመታት ውስጥ የባህር ኃይል አባል ሆኖ በቬትናም ሁለት ጊዜ ተልኮ ግዴጅ የፈጸመ እና የእሳት አደጋ ሰራተኛ ሆኖ ያገለገለ ነው። ሊዩስ ልጆች አፍርቶ የልጅልጅ ለመሳም በቅቷል።
ሊዩስ እና ወንድሙ መገናኘታቸው ቢያስደስታቸውም፣ ሮገር ከወራት በፊት የካንሰር ህክምና ማድረጉ ደግሞ የሀዘን ድባብ ፈጥሮባቸዋል።
"ረዘም ላለ ጊዜ ተቃቀፉ፤ ቁጭ ብለውም አወሩ" ትላለች አሊዳ።
ሮገር ባለፈው ነሐሴ ወር ህይወቱ ከማለፉ በፊት ሁለቱ ወንድማማቾች መገናኘት የቻሉት ሁለት ጊዜ ብቻ ነበር።
አሊዳ "በሰላም ህይወቱ አልፏል ብየ አስባለሁ። ወንድሞ በህይወት እንዳለ ካወቀ በኋላ በመሞቱ ለራሱ ሰላም ይሰጠዋል። እኔም ይህን በማድረጌ በጣም ደስተኛ ነኝ"ስትል ተናግራለች።