አቡ ዳቢ 'የኃይማኖት አባቶችና መሪዎች በአየር ንብረት' በሚል ርዕስ ዓለም አቀፍ ጉባኤ ልታስተናግድ ነው
ጉባኤው ከዓለም የአየር ንብረት ጉባኤ (ኮፕ28) በፊት ይካሄዳል
ጉባኤው በኃይማኖትና በሳይንስ መካከል ትብብር ለመፍጠርና በሁለቱ መካከል ያለውን ልዩየት ለማጥበብ ዓላማ ሰንቋል
በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ፕሬዝዳንት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አል ነህያን አነሳሽነት ከመላው ዓለም የተውጣጡ የኃይማኖት አባቶችና መሪዎች በአየር ንብረት ላይ በአቡዳቢ ሊመክሩ ነው።
ጉባኤው በጎረጎሮሳዊያኑ ከህዳር 5 እስከ 6 የሚካሄድ ሲሆን፤ ዓላማውም በአየር ንብረት ለውጥ እርምጃዎች ላይ ኃይማኖት ያለውን ስፍራ ለማስገንዘብ ነው።
ጉባኤው ከዓለም የአየር ንብረት ጉባኤ (ኮፕ28) በፊት ይካሄዳል።
የኤምሬትስ የዜና አገልግሎት እንደዘገበው የዓለም ግዙፍ የኃይማኖት ተቆማትን የወከሉ አባቶችና መሪዎች፣ ሙህራንና ባለሞያዎች የአየር ንብረት የሙስሊም ሽማግሌዎች ም/ቤት የኮፕ28 ፕሬዝዳንት፣ ከመንግስታቱ ድርጅት የአየር ንብረት መርሀ-ግብር፣ ከካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን በመተባበር ባዘጋጁት ጉባኤ ይሳተፋሉ።
ጉባኤው የአየር ንብረት ላይ ኃላፊነትን ለመወጣት የኃይማኖት ተቋማት ሚና ላይ ያተኩራል።
በተጨማሪም ጉባኤው በኃይማኖትና በሳይንስ መካከል ትብብር ለመፍጠርና በሁለቱ መካከል ያለውን ልዩየት ለማጥበብ ዓላማ ሰንቋል።
ኮፕ28 በዱባይ ኤግዚቢሽን ማዕከል በፈረንጆች ከህዳር 30 እስከ ታህሳስ 10 የሚካሄድ ሲሆን፤ የሀገራት መሪዎች፣ ባለስልጣናት፣ ዓለም አቀፍ ተቋማት፣ ሙህራንና ባለሞያዎችን ጨምሮ 70 ሽህ የሚጠጉ ሰዎች ይሳተፉበታል ተብሎ ይጠበቃል።