የ2030ዋ ዓለም ዋንጫ በስፔን ፖርቹጋል እና ሞሮኮ አስተናጋጅነት እንደሚካሄድ ይጠበቃል
አፍሪካ እና አውሮፓ በባቡር ትራንስፖርት ሊገናኙ ነው ተባለ
አፍሪካ ከአፍሪካ ጋር እስካሁን በቀጥታ የሚያገናኝ የየብስ ትራንስፖርት የሌለ ሲሆን በሞሮኮ በኩል ሁለቱን አህጉራት የሚያገናኝ ትራንስፖርት ለመገንባት ጥረት መጀመሩን ዩሮ ኒውስ ዘግቧል፡፡
እንደ ዘገባው ከሆነ ሞሮኮ እና ስፔን በጋራ የባቡር ትራንስፖርት መሰረተ ልማቱን ለመገንባት ጥረት የጀመሩ ሲሆን ሁለቱ ሀገራት የየብስ ትራንስፖርት ለመጀመር ካሰቡ 45 ዓመት ሞልቷቸዋል፡፡
የ2030 የዓለም ዋንጫን በጋራ ለማዘጋጀት ለፊፋ ጥያቄ ያቀረቡት ስፔን ፖርቹጋል እና ሞሮኮ የባቡር ትራንስፖርቱን በ5 ዓመታት ውስጥ ለማጠናቀቅ እቅድም ይዘዋል ተብሏል፡፡
ኢትዮጵያ በአውሮፓ ህብረት ውሳኔ ማዘኗን ገለጸች
የስፔን ባለስልጣናት ወደ ሞሮኮ በተደጋጋሚ በማምራት የባቡር መሰረተ ልማቱ ግንባታ እንዲጀመር የሁለትዮሽ ውይይቱ በመጠናቀቅ ላይ ስለመሆኑም ተገልጿል፡፡
ስፔን በራሷ በኩል ያለውን የባቡር መስመር ለመገንባት 2 ነጥብ 3 ቢሊዮን ዩሮ መመደቧን ስትገልጽ የሞሮኮ ድርሻ እስካሁን ይፋ አልሆነም ተብሏል፡፡
የባቡር ትራንስፖርት መስመሩ ታንጀር ከተሰኘችው የሞሮኮ ወደብ ዳርቻ ተነስቶ ማድሪድ ለመድረስ 300 ኪሎ ሜትር እንደሚረዝምም ተገልጿል፡፡
የባቡር መስመሩ ግንባታ ከተጠናቀቀ ከማድሪድ ካዛብላንካ ለመጓዝ 5 ሰዓት ከግማሽ ጊዜ ይፈጃልም ተብሏል፡፡
አፍሪካን ከአውሮፓ ጋር በየብስ በማስተሳሰር የመጀመሪያ ይሆናል የተባለው ይህ የባቡር ትራንስፖርት ወጪ በሁለቱ ሀገራት ይሸፈናል የተባለ ሲሆን ግንባታው በቅርቡ እንደሚጀመር ይጠበቃል፡፡