የተሻለ ወርሀዊ ደመወዝ የሚከፈልባቸው የአፍሪካ ሀገራት የትኞቹ ናቸው?
ሲሸልስ ሊቢያ እና ሞሮኮ በአንጻራዊነት የተሸለ ደመወዝ የሚከፍልባቸው ሀገራት ናቸው
በኢትዮጵያ አማካኝ ወርሃዊ ደመወዝ 150 ዶላር ነው
የተሻለ ወርሀዊ ደመወዝ የሚከፈልባቸው የአፍሪካ ሀገራት የትኞቹ ናቸው?
የዓለም ላብ አደሮች ወይም ሰራተኞች ቀን በየዓመቱ ሚያዝያ 23 ቀን የሚከበር ሲሆን የዘንድሮውም በዓል ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ ዝግጅቶች በመከበር ላይ ይገኛል፡፡
እንደ ዓለም አቀፉ የስታትስቲካ ጥናት ከሆነ በአፍሪካ ሲሸልስ ሊቢያ እና ሞሮኮ በአንጻራዊነት የተሻለ ደመወዝ የሚከፍሉ ሀገራት ናቸው፡፡
በሲሸልስ አንድ ሰራተኛ በአማካኝ በወር 432 ዶላር ደመወዝ ሲከፈል በሊቢያ 322 ዶላር እንዲሁም በሞሮኮ ደግሞ 281 ዶላር ይከፈላል፡፡
ሌላኛዋ አፍሪካዊት የተሻለ ደመወዝ ከፋይ ሀገር ጋቦን ስትሆን 256 ዶላር በወር ለአንድ ሰራተኛ ስትከፍል ደቡብ አፍሪካ፣ ሞሪሺየስ እና ኢኳቶሪያል ጊኒ 200 ዶላር እና ከዛ በላይ የሆነ ገንዘብ ለሰራተኞቿ ትከፍላለች ተብሏል፡፡
እንደ ወርልድ ሳላሪ ድረገጽ መረጃ ከሆነ በኢትዮጵያ አንድ ሰራተኛ በአማካኝ 150 ዶላር የሚከፈለው ሲሆን በዓመት ደግሞ 1 ሺህ 800 ዶላር ይከፈላቸዋል፡፡
የመንግስት ተቋማት፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን እና ሌሎች ዓለም አቀፍ ተቋማት የደመወዝ አከፋፈል ስርዓቶችን እና ጥናቶችን ዋቢ አድርጎ መረጃ መሰብሰቡን የገለጸው ወርልድ ሳላሪ ድረገጽ በኢትዮጵያ ከ2 ሺህ ብር ጀምሮ እስከ 470 ሺህ ብር ድረስ ወርሀዊ ደመወዝ ይከፈላል ብሏል፡፡