ከፍተኛ የእድሜ ጣራ ያስመዘገቡ 10 የአፍሪካ ሀገራት የትኞቹ ናቸው?
በአፍሪካ አማካኝ የእድሜ ጣራ በፈረንጆቹ 2000 እስከ 2019 ባለው ጊዜ ከ46 ወደ 56 ከፍ ብሏል
76.4 ዓመት አማካኝ የእድሜ ጣራ ያስመዘገበችው አልጄሪያ ቀዳሚውን ስፍራ ይዛለች
የዓለም ባንክ በአፍሪካ ያለው የሰዎች አማካኝ የእድሜ ጣሪያ ለተከታታይ 10ኛ ዓመት እድገት ማሳየቱን በያዝነው ወር ባወጣው ሪፖርት አመላክቷል።
በአፍሪካ ያለው የእድሜ ጣራ ከስፍራ ስፍራ ከፍተኛ የሆነ ልዩነት ያለው ሲሆን፤ ለልዩነቱ ዋነኛ ምክንያቶችም የጤና አገልግሎት ተደራሽነት፣ የኢኮኖሎ እድገት እና የበሽታ መስፋፋት ተጠቃሽ ናቸው።
እንደ ዓለም ባንክ ሪፖርት ከሆነ በአፍሪካ ከከፍተኛው እስቀ ዝቅተኛው የእድሜ ጣሪያ ያለ ሲሆን፤ ቀጥሎ የተዘረዘሩ 10 ሀገራት እንደ ቅደም ተከተላቸው ከፍተኛው የእድሜ ጣሪያ የተመዘገበባቸው ሀገራት ናቸው።