በአዕምሮ ምጥቀት (አይኪው) ቀዳሚ የአፍሪካ ሀገራት
ችግርን የመፍታት አቅም፣ የማስታወስ ችሎታ፣ ምክንያታዊነት እና የቋንቋ ክህሎት የአዕምሮ ምጥቀት መለኪያ ናቸው
የአዕምሮ ምጥቀት (አይኪው) ፈተናዎች ምዕራባውያንን ብቻ ያማከሉ ናቸው በሚል ይተቻሉ
የአዕምሮ ምጥቀት (ኢንተለጀንስ ኮሸንት) ጉዳይ ለመጀመሪያ ጊዜ የተነሳው በአልፍሬድ ቢኔት አማካኝነት ነው።
አልፍሬድ ተማሪዎች በትምህርታቸው ላይ ድጋፍ ይፈልጉ እንደሆን ለማወቅ ያለመ ፈተና እንዲያዘጋጅ በመንግሥት ታዞ ነበር።
የአእምሮ ምጥቀት ፈተናዎች ችግርን የመፍታት አቅም፣ የማስታወስ ችሎታ፣ ምክንያታዊነት እና የቋንቋ ክህሎት የሚለኩ ናቸው።
በፈረንጆቹ 1995 ወደ አሜሪካ ለመምጣት ሙከራ የሚያደርጉ ስደተኞች የአእምሮ ምጥቀት ፈተና ይሰጣቸው እንደነበር መረጃዎች ያወሳሉ።
የአእምሮ ምጥቀትን ከብልህነት ጋር አቻ አድርጎ መውሰድና መለኪያ ፈተናዎቹም ምዕራባውያንን ብቻ ያማከሉ መሆናቸው ቅሬታን ሲያስነሳ ይታያል።
ብልህነት በነጠላ ቁጥር ከሚመዘነው የአዕምሮ ምጥቀት ምዘና በእጅጉ የተለየና የተወሳሰበ ነገር መሆኑን የሚገልጹ ባለሙያዎች በተለያዩ ተቋማት የሚወጡ ጥናቶችን ውድቅ ሲያደርጓቸው ይስተዋላል።
ሪቻርድ ሌን እና ዴቪድ ቤከር ባወጡት ሪፖርት የአዕምሮ ምጥቀት ምዘናው የሀገራትን የእድገት ደረጃ፤ የዜጎቻቸውን የማስተዋል አቅም እንደሚያመላክ በመጥቀስ ይሞግታሉ።
በሪፖርታቸው ከአፍሪካ በአዕምሮ ምጥቀት (አይኪው) ቀዳሚ ናቸው ያሏቸውን 10 ሀገራት ዘርዝረዋል።