ዝቅተኛ የኤሌክትሪክ ሽፋን ያላቸው 10 የአፍሪካ ሀገራት
ከፍተኛ የሀይል አቅርቦት ችግር ባለባት አፍሪካ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶችን ለመገንባት የበጀት እጥረት ፈተና ሆኗል
1.3 ቢሊዮን ህዝብ በሚገኝባት አህጉር 600 ሚሊዮን ሰዎች የኤሌክትሪክ አገልግሎት አያገኙም
1.3 ቢሊዮን ህዝብ በሚገኝባት አህጉር 600 ሚሊዮን ሰዎች የኤሌክትሪክ አገልግሎት አያገኙም።
ከፍተኛ የሀይል አቅርቦት ችግር ባለባት አፍሪካ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶችን ለመገንባት የበጀት እጥረት ፈተና ሆኗል
በአፍሪካ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ሽፋን ምጣኔ በ43 በመቶ ብቻ የሚለካ ነው። በማደግ ላይ ባለችው አህጉር ኢንዱስትሪዎችን ለማንቀሰቃስ እና የውጭ ባለሀብቶችን ለመሳብ የሀይል አቅርቦት ወሳኝ ቢሆንም የአቅርቦት እጥረቱ ከፍተኛ ነው፡፡
የአፍሪካ ሀገራት የድንጋይ ከሰል፣ ለሀይድሮ ኤሌክትሪክ ማመንጫ ሊውሉ የሚችሉ ወንዞች እና የተፈጥሮ ነዳጅ ባለጸጋ ቢሆኑም እነዚህን ጸጋዎች ወደ ፕሮጀክት ቀይሮ ሀይል ማመንጨት ላይ ከፍተኛ የበጀት እጥረት ፈተና ሆኖባቸዋል፡፡
በዚህ የተነሳም 600 ሚሊዮን በከተማ እና በገጠር የሚኖሩ ዜጎች በመሰረታዊ የሀይል አቅርቦት ችግር ውስጥ ህይወታቸውን እንዲገፉ ተገደዋል፡፡
በዚህ የሀይል አቅርቦት እጥረት መኖርያ ቤቶች፣ጤና ተቋማት፣ትምህርት ቤቶች እና በአጠቃላይ ኢኮኖሚው ችግር ውስጥ ይገኛል፡፡
አለም አቀፉ የኢነርጂ ኤጄንሲ በአፍሪካ በርካታ ህዝባቸው የኤሌክትሪክ አገልግሎት የማያገኙ ሀገራት በሚል ባወጣው ዝርዝር ናይጄሪያ 86 ሚልየን ዜጎቿ ኤሌክትሪክ አያገኙም ሲል በቀዳሚነት አሰቀምጧታል። ዲ አር ኮንጎ ሁለተኛ ስትሆን ኢትዮጵያ በሶስተኛ ደረጃ ትገኛለች፡፡
በርካታ ህዝባቸው የኤሌክትሪክ አገልግሎት የማያገኙ 10 የአፍሪካ ሀገራትን ዝርዝር ከስር ካለው ምስል ይመልከቱ።