ኤጀንሲው ከዛሬ ጀምሮ የጥሬ ገንዘብ ግብይትን ውል አልፈጽምም አለ
ውል ለመፈጸም ባንክ ከሚገኝ የገዢ ሒሳብ ተቀናሽ ሆኖ ወደ ሻጭ የባንክ ሒሳብ መተላለፍ አለበት ተብሏል
የባንክ ኖት መቀየሩን ተከትሎ ስነዶች ማረጋገጫ ኤጀንሲ የጥሬ ገንዘብ ግብይትን ውል አልፈጽምም አለ
የባንክ ኖት መቀየሩን ተከትሎ ስነዶች ማረጋገጫ ኤጀንሲ የጥሬ ገንዘብ ግብይትን ውል አልፈጽምም አለ
ከዛሬ ጀምሮ ንብረት በጥሬ ገንዘብ መግዛትና መሸጥ እንደማይቻል የፌዴራል ሰነዶች መረጋገጫ እና ምዝገባ ኤጀንሲ አስታወቀ።
ኤጀንሲው በይፋዊ የፌስቡክ ገጹ እንዳሰፈረው የብር ኖቶችን ለውጥ ተከትሎ ከዛሬ መስከረም 7 ቀን 2013 ጀምሮ የሚንቀሳቀስም ሆነ የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ ውል እንዲሁም የብድር ውሎችን ሰነድ አረጋግጦ የመመዝገብ አገልግሎት ለማግኘት ወደ ኤጀንሲው የሚመጡ ተገልጋዮች የሽያጭ ዋጋ ወይም የብድሩ ገንዘብ አከፋፈልን በተመለከተ ክፍያው መፈጸም ያለበትን መንገድ ይፋ አድርጓል።
በሽያጭ ውል ጊዜ የሽያጭ ዋጋው ባንክ ከሚገኝ የገዢ ሒሳብ ተቀናሽ ሆኖ ወደ ሻጭ የባንክ ሒሳብ የተላለፈ መሆን እንዳለበትም ኤጀንሲው አስፍሯል፡፡
የሚንቀሳቀስም ሆነ የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ ውል እንዲሁም የብድር ውሎችን ሰነድ አረጋግጦ የመመዝገብ አገልግሎት ለማግኘት ወደ ኤጀንሲው የሚመጡ ተገልጋዮች የሽያጭ ዋጋ ወይም የብድሩ ገንዘብ አከፋፈልን በተመለከተ ክፍያው መፈጸም አለባቸውም ተብሏል፡፡
በሽያጭ ውል ጊዜ የሽያጭ ዋጋው ባንክ ከሚገኝ የገዢ ሒሳብ ተቀናሽ ሆኖ ወደ ሻጭ የባንክ ሒሳብ የተላለፈ መሆን ያለበት ሲሆን በብድር ውል ጊዜ የብድሩ ገንዘብ ባንክ ከሚገኝ የአበዳሪ ሒሳብ ተቀናሽ ሆኖ ወደ ተበዳሪ የባንክ ሒሳብ የተላለፈ መሆን አለበት ብሏል፡፡
በመሆኑም የሽያጩ ዋጋ ወይም የብድሩ ገንዘብ ክፍያው ከላይ በተገለጸው አግባብ የተፈጸመ ስለመሆኑ የሚገልጽና በባንኩ ማኅተም የተደገፈ የሒሳብ ማስተላለፊያ የሰነድ ማስረጃ መቅረብ እንደሚገባ ኤጀንሲው አስታውቋል፡፡
ሕገ ወጥነትን ለመከላከል ሲባል ሌሎች የአሠራር ማሻሻያዎች እስኪደረጉ ድረስ የሚንቀሳቀስም ሆነ የማይንቀሳቀ ንብረትን በስጦታ የማስተላለፍ ውል አረጋግጦ የመመዝገብ አገልግሎት ኤጀንሲው ላልተወሰነ ጊዜ እንደማይሰጥ ገልጿል፡፡