በአሜሪካ የተሰጠውን ተልእኮ እንዲያቋርጥ ያደረገ ኦፕሬተሮቹን የገደለው ሮቦት ድሮን
ድሮኑ የአውሮፕላን ኦፕሬተሩን ተኩሶ የገደለው ከማሳካው ተልዕኮ አግዶኛል በሚል ነው
የአሜሪካ አየር ሀይል በበኩሉ ኦፕሬተሩ በድሮን ተገደለ የሚለውን መረጃ ውድቅ አድርጓል
በአሜሪካ አየር ሀይል የተሰራ እና በአርቴፊሻ ኢንተለጀንስ የሚታዘዝ ሮቦት ድሮን ኦፕሬተሩን ገደለ።
በሀገረ አሜሪካ አየር ኃይል የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ የተገጠመለት ምስለ በረራ ልምምድ ባደረገበት ወቅት አነጋጋሪ ክስተት ማጋጠሙ ተገልጿል።
የአየር ሀይል ድሮን በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ታግዞ ባደረገው ልምምድ ላይ ኦፕሬተሩ ድሮኑ ድርጊቱን ለማስቆም ሲሞክር እንደተኮሰበት ተገልጿል።
እንደ ዘጋርዲያን ዘገባ ከሆነ ድሮኑ ወደ ኦፕሬተሩ የተኮሰበት ከተልዕኮዬ ሊያሰናክለኝ ነው በሚል ነው።
በአሜሪካ አየር ሀይል የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሙከራ ሀላፊ የሆኑት ሀሚልተን እንዳሉት በወቅቱ ድሮኑ የተሰጠው ተልዕኮ የጠላትን የአየር ሀይል መሰረተ ልማት እንዲያወድም የነበረ ሲሆን ይህ ድሮን ይህን ተልዕኮ ከመፈጸም እንዲያቆም በኦፕሬተሩ ሲጠየቅ ተኩስ ከፍቷል ብለዋል።
ሀላፊው አክለውም ሮቦቱን ማሳካት የሚፈልገውን ተልዕኮ እንዲያሳካ ማንኛውንም አይነት እርምጃ እንዲወስድ አሰልጥነነዋል ብለዋል።
በመሆኑም ለሮቦቶች ስለ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ስነ ምግባር ማሰልጠን ይኖርብናል ሲሉም ሀላፊው ተናግረዋል።
የአሜሪካ አየር ሀይል ቃል አቀባይ አን ስቴፋኔክ በበኩላቸው ዋሽንግተን ሮቦትንም ሆነ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስን በሀላፊነት እየተጠቀመች ነው ብለው ተገደለ ያተባለው ኦፕሬተር ሀሰት መሆኑን ተናግረዋል።
በአሜሪካ አየር ሀይል የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሙከራ ሀላፊ የሆኑት ሀሚልተን የምስለ በረራ ልምምዱ በሮቦት እና አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ መካከል የተካሄደ እንጂ የሰው ልጅ እንዳልነበር እና የተጎዳም ሰው አለመኖሩን ጠቅሰዋል።