የዓለማችን ኮምፒውተር ጠበብቶች ለምን የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስን ተጠራጠሩት?
የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ አባት የሚባሉት ዮሺዋ ቤንግዮ ቴክኖሎጂ የሰውን ልጅ ወደ አላስፈላጊነት ሊለውጥ እንደሚችል ተናገሩ
የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ አባት የሚባሉት ዮሺዋ ቤንግዮ ቴክኖሎጂ የሰውን ልጅ ወደ አላስፈላጊነት ሊለውጥ እንደሚችል ተናገሩ
የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ አባት የሚባሉት ዮሺዋ ቤንግዮ አሁን እየወጡ ስላሉ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ ፈጠራዎች ዙሪያ ከቢቢሲ ጋር ቆይታ አድርገዋል።
ይህ የዓለማችን ቴክኖሎጂ ብዙዎችን እያስደመመ ቢሆንም ስጋትነቱ እያየለ በመምጣት ላይ ይገኛል።
የቡድን ሰባት ሀገራት ባሳለፍነው ሳምንት በጃፓን ሂሮሺማ ከተማ በተሰበሰበበት ወቅት የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ ዋነኛ የመወያያ አጀንዳው ነበር።
ቴክኖሎጂው የሰውን ልጆችን ህይወት በማቅለል ረገድ ጥሩ ነው የሚባል ቢሆንም የሰዎችን ህይወት ሊያወሳስብ እና ሊጎዳ የሚችሉ ስራዎች ሊሰሩበት ይችላሉ የሚለው አስተያየት እያየለ መጥቷል።
የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ አባት በመባል የሚታወቁት የኮምፒውተር ሊቁ ፕሮፌሰር ዮሺዋ ቤንግዮ አርቲፊሻል ቴክኖሎጂ በጥንቃቄ ካልተያዘ ለመቆጣጠር አዳጋች የሖነ ጅምላ ጨራሽ ኬሚካል በቤተ ሙከራ ውስጥ ሊፈጠር ይችላል ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
ይህም ሰዎች ከምድረ ገጽ እንዲጠፉ ሊያደርግ ይችላል የተባለ ሲሆን አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ጥብቅ ቁጥጥር ሊደረግበት እንደሚገባ ባለሙያው ጠቁመዋል።
ወታደራዊ ተቋማት የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ ሊጠቀሙ እንደማይገባ የጠቆሙት ፕሮፌሰር ቤንጊዮ ቴክኖሎጂው ዓለማችንን ወደ አላስፈላጊ ፉክክር እና ህግ ጥሰቶች ሊወስዳት ይችላልም ብለዋል።
ከዚህ በፊት ኮምፒተር ስራዎችን በፍጥነት እና በጥራት እንዲሰሩ የሰው ልጆች ያስፈልጉ ነበር አሁን ግን ቴክኖሎጂው ያለሰው ልጆች መስራት መጀመራቸው አደገኛ መሆኑን ባለሙያው ጠቅሰዋል።
እንደ ፕሮፌሰር ቤንግዮ ስጋት ቴክኖሎጂው የፈጠረውን እድል በመጠቀም ሰዎች እጅግ ገዳይ የኬሚካል ጦር መሳሪያ በቀላሉ ሊፈጥሩ ይችላሉ።
አንዴ ይህ ገዳይ ጅምላ ጨራሽ ኬሚካል ከተፈጠረ ደግሞ ለመከላከል እና ለመቆጣጠር አዳጋች ሁኔታዎች ሊፈጠሩ እና የሰው ልጆች አደጋውን ከመቀበል ውጪ አማራጭ ላይኖራቸው አንደሚችልም ባለሙያው አስጠንቅቀዋል።
በርካታ የዓለማችን የኮምፒውተር ጠበብቶች በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ፍጥነት መጨነቃቸውን እና ቴክኖሎጂው በመጥፎ ሰዎች እጅ ላይ ከወደቀ በዓለም ላይ ችግር እንደሚፈጠር በማስጠንቀቅ ለይ ናቸው።
በመሆኑም መንግስታት አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ የሚጠቀሙ ሰዎችን እና ተቋማትን በግልጽ መመዝገብ እና መታወቅ አለባቸው ሲሉም በመናገር ላይ ናቸው።
ይህ የዓለማችን የዘመኑ ቴክኖሎጂ የሰው ልጆችን በቁጥጥር ስር በማዋል ቀስ በቀስ የሰው ልጆችን ወደ አላስፈላጊነት ሊለውጥ እንደሚችልም አስግቷል።
አርቲፊሻል ቴክኖሎጂ ልክ እንደ አየር ንብረት ለውጥ ለዓለም ስጋት መሆኑን በመገንዘብ እና ጉዳቶችን መቀነስ የሚያስችሉ ስርዓቶች መዘርጋት እንዳለበት ተገልጿል።