ኦማር አልበሽር ለ1989ኙ መፈንቅለ መንግስት ተጠያቂ ነኝ አሉ
የሱዳን የቀድሞው ፕሬዝዳንት አልበሽር ከስልጣን ከተወገዱ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ምስክርነት ተሰጥተዋል
መፈንቅለ መንግስቱ በሱዳን ጦር በዲሞክራሲ በተመረጡት ጠቅላይ ሚንስትር ሳዲቅ አል-መሀዲ ተካሂዷል
ከስልጣን የተወገዱት የሱዳኑ ፕሬዝዳንት ኦማር አልበሽር በፈረንጆቹ ሰኔ 30 ቀን 1989 የሳዲቅ አል-ማህዲንን መንግስት ለጣለው መፈንቅለ መንግስት ሙሉ ኃላፊነት እንደሚወስዱ በፍ/ቤት ፊት አስታውቀዋል።
አልበሽር ከስልጣን ከተወገዱ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በፍ/ቤት ፊት በሰጡት ምስክርነት “ሁኔታው ምንም ሊዘገይ አልቻለም። መንግስት ምላሽ ሊሰጣቸው የሚገቡ ልዩ ጉዳዮች ነበሩ" በማለት ስለ መፈንቅለ መንግስቱ ጥንሰሳ ተናግረዋል።
አክለውም የቀድሞው ፕሬዝዳንት "ለመንግስት የአንድ ሳምንት ማስታወቂያ ሰጠን። ነገር ግን ምንም አልተፈጠረም። ይህም በታጣቂ ኃይሎች ውስጥ ከፍተኛ ቅሬታን ፈጠረ። በጣም ንቁ የሆነ የመኮንኖች እንቅስቃሴ በሱዳን ያለውን ሁኔታ መለወጥ ጀመረ" ብለዋል።
በመቀጠልም "እኛ ከእነዚህ ቡድኖች ውስጥ አንዱ ነበርን። ጉዳዩ መስዋዕትነትን ይጠይቃል። ጠቅላይ እዝ ውስጥ ስንገባ የጦር ኃይል ይዘን አልገባንም። ጠባቂ መስዬ ገባሁ። ምላሹ ፈጣን እና ያለምንም ማመንታት ነበር" በማለት ሁነቱን አስረድተዋል።
"[በፈረንጆቹ ] ሰኔ 30 ላይ ለተፈጠረው ነገር እኔ ሁሉንም ሀላፊነት እሸከማለሁ። እናም መናዘዝ ለማስረጃ ሁነኛ እንደሆነ አውቃለሁ” በማለት ንግግራቸውን አጠቃለዋል።
መፈንቅለ መንግስቱ በሱዳን ጦር በዲሞክራሲ በተመረጡት ጠቅላይ ሚንስትር ሳዲቅ አል-መሀዲ ተካሂዷል።
አልበሽር 15 የጦር ኃይል መኮንኖች እና ስምንት ሲቪሎች ከሰኔ 30ው 1989 መፈንቅለ መንግስት ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን በመናድ የሞት ቅጣት የሚያስቀጣ ክስ ለመመስረት በልዩ ፍርድ ቤት ቀርበዋል።