ጋንዱርና እና ሌሎች 12 ሰዎች በመፈንቅለ መንግስት ሙከራና እና አመጽ በማነሳሳት ተከሰው ነበር የታሰሩት
ሱዳን በትናንትናው እለት የፈረሰው የናሽናል ኮንግረስ ፓርቲ ኃላፊ የሆኑትን ኢብራሂም ጋንዱርን እና ሌሎችን ሰዎችን ከእስር ለቃለች፡፡
ኢብራሂም ጋንዱር ፕሬዝዳንት ኦማር አልበሽር ስልጣን ላይ በነበሩበት ወቅት የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው ያገለገሉ ናቸው፡፡
ፍድርቤቱ የፓርቲውን የሚሊሻ ኃላፊ እና የብጥብጥ መሪ ነበር የተባለውን አናስ ኦማርን ጨምሮ ከአይኤስ አይኤስ ጋር ግንኙነት አለው ተብሎ የተከሰሰውን ሙሃመድ አሊ አል ጆዝሊን ለቋል፡፡
እስረኞቹ የተለቀቁት፣ፍርድቤቱ ጋንዱርን እና ሌሎች 12 የፓርቲው የቅርብ ሰዎች ላይ ቀርበው የነበሩትን የሽብርተኝነት፤ የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ እና ብጥብጥ የማስነሳት ክሶችን በማቋረጡ ነው፡፡
ጋንዱር የናሽናል ኮንግረሽ ፓርቲ መሪ ሆነው ከመሾማቸው በፊት፣በቤተመንግስት የፕሬዝደንት አልበሽር ረዳት እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ነበሩ፡፡ ጋንዱር ፓርቲውን እንዲመሩ የተሾሙት፤ ፓርቲው በሀገሪቱ በፈረንጆቹ ሚያዚያ 2019 በህዝባዊ አመጽ ከስልጣን ከተወገደ በኋላ ነበር፡፡
የፓርቲው አባልት ከእስር ለተፈቱት ኃላፊው መልካል ምኞታቸውን አቅርበዋል፡፡ ጋንዱርና እና ሌሎች 12 ሰዎች በፈረንጆቹ 2020 በመፈንቅለ መንግስት ሙከራና እና አመጽ በማነሳሳት ተከሰው ነበር የታሰሩት፡፡