አልበሽር ከ31 አመታት በፊት በመሩት መፈንቅለ መንግስት ተከሰሱ
የሱዳን ፍርድቤት ባለፈው ታህሳስ ወር በሙስና ክስ የሁለት አመት እስር አስተላልፎባቸው ነበር
አልበሽር ስልጣን በያዙበት የፈረንጆቹ 1989 መፈንቅለ መንግስት ተከሰሱ
አልበሽር ስልጣን በያዙበት የፈረንጆቹ 1989 መፈንቅለ መንግስት ተከሰሱ
በህዝባዊ ተቃውሞ ምክንያት ከስልጣን የተወገዱት የቀድሞው የሱዳን ፕሬዘዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽርና አጋሮቻቸው በፈረንጆቹ 1989 ባካሄዱት እሳቸውን ወደ ስልጣን ባመጣው መፈንቅለ መንግስት ተከሰሱ፡፡
የሱዳን ፍርድቤት ባለፈው ታህሳስ ወር በሙስና ክስ የሁለት አመት እስር አስተላልፎባቸው ነበር፡፡ አልበሽር በሰልፈኞች ግድያ እጃቸው አለበት በሚል ተከሰው ምርመራ እየተካሄደባቸው ይገኛል፡፡
አልበሽር ክስ ካርቱም በሚገኝ ፍርድቤት የተከፈተ ሲሆን አልበሽር ግን አለመታየቱን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡ ባለፈው አመት በህዝብ ተቃውሞ ከወረዱ በኋላ በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡ባለፈው ታህሳስ ወር የአልበሽር ጠበቃ በአልበሽር ላይ የተመሰረተው ክስ ፖለቲካዊ ነው ብሎ ነበር፡፡
በፍርድቤቱ ውሎው ምንም አይነት መረጃ ሳይቀርብ፤ ጉዳዩ ለፈረንጆቹ ነሀሴ 11 እንዲታይ የተቀየረ ሲሆን ይህ የሆነው ሰፊ በሆነ ፍርድቤት ጠበቆችና የተከሳሽ ቤተሰብ አባላት እንዲሳተፉ ለማድረግ መሆኑ ተነግሯል፡፡አንድአንድ የህግ ባለሙያዎች የዛሬውን ችሎት መግባት ባለመቻላቸው ቅሬታ አቅርበዋል፡፡
የአልበሽር አጋር ተብለው የተከሰሱት ደግሞ የቀድሞው ምክትል ፕሬዘዳንት አሊ ኦስማን ጠሃ እና አሊ አልሃጂ የእስላማዊ ፖፑላር ኮንግረስ ጸኃፊ መሆናቸውን ባለስልጣናት ገልጸዋል፡፡
አልበሽር ከስልጣን ከተወገደ በኋላ ሀገሪቱ ከወታደሩና ከህዝቡ በተወከሉ ሰዎች ስር ሆና በሽግግር መንግስት እየሰራች ትገኛለች፡፡
እስላማዊው የአልበሽር ፓርቲ በሀገሪቱ እየተካሄደ ባለው የሽግግር ሂደት አልተካፈልኩም ተገልያሉሁ በማለት ቅሬታ አስምቷል፡፡
ባለፈው አርብ እለት በመቶዎች የሚቆጠሩ የእስላማዊ ፓርቲ ደጋፊዎች፣ መንግስት ለበርካታ አስርት አመታት የቆየውን ህግ በመሻር እስላም ያልሆነ ሰዎች አልኮል እንዲጠጡ መፍቀዱን ተከትሎ ሰልፍ ወጥተው ተቃውሟቸውን አሰምተው ነበር፡፡