
ሁለት አጥፍቶ ጠፊዎች ቦምብ ያፈነዱት በገበያ ስፍራ ላይ ነው
በኢራቅ መዲና ባግዳድ ሁለት አጥፍቶ ጠፊዎች ባፈነዱት ቦምብ እስካሁን 28 ሰዎች መገደላቸውን የሀገሪቱ ባለሥልጣናት አስታወቁ፡፡
ፍንዳታው የተከሰተው በባግዳድ የገበያ ማዕከል አካባቢ ሲሆን በአደጋው የሟቾች ቁጥር ከዚህም እንደሚያሻቀብ ተገልጿል፡፡
በመዲናዋ በደረሰው ጥቃት ከሟቾች በተጨማሪም እስካሁን 73 ሰዎች መጎዳታቸው መረጋገጡን የተለያዩ ሚዲያዎች ዘግበዋል፡፡
የኢራቅ የሀገር ውስጥ ሚኒስቴር ከጥቃት አድራሾች መካከል አንደኛው የታመመ በመምሰል ሰዎች እንዲሰበሰቡ ሲያደርግ እንደነበር ገልጸዋል፡፡ የሰዎቹን መሰብሰብ ተከትሎ ቦምብ ማፈንዳቱንም ነው የገለጹት፡፡
ከአውሮፓውያኑ 2017 በኋላ በባግዳድ እንደዚህ አይት ጥቃት ለመጀመሪያ ጊዜ ነው የተፈጸመው፡፡
ለጥቃቱ ኃላፊነቱን የወሰደ አካል ባይኖርም አይኤስ ሳይፈጽመው እንዳልቀረ ግን ተገምቷል፡፡
አይኤስ እ.ኤ.አ በ2017 መሸነፉ ቢታወጅም የቡድኑ አባላት እስካሁን ድረስ የተለያዩ ጥቃቶችን መፈጸማቸውን ቀጥለዋል፡፡