ኢራቃውያን የአሜሪካ ጦር ከሀገሪቱ ለቆ እንዲወጣ በአደባባይ ጠየቁ፡፡
በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢራቃውያን ባግዳድ በሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ አቅራቢያ በመሰባሰብ የአሜሪካ ጦር ከሀገሪቱ ለቆ እንዲወጣ ጠይቀዋል፡፡
በሰልፉ ላይ በኢራን የሚደገፈው ታጣቂ ሀይልም ተሳታፊ ሆኗል፡፡
ጥር 3 አሜሪካ በወሰደችው የአየር ጥቃት የኢራኑ ከፍተኛ የጦር መሪ ቃሲም ሱሌይማኒ መገደላቸውን ተከትሎ በሀገራቱ መካከል የነበረው ቅራኔ ተባብሷል፡፡
ለዚህ አፀፋ ኢራን ሁለት የባለስቲክ ሚሳይሎችን ኢራቅ በሚገኘው የአሜሪካ የጦር ካምፕ ላይ በማሰወንጨፏ በአሜሪካ ወታደሮችና ንብረት ላይ ጉዳት መድረሱ ይታወሳል፡፡
ይህ ሁኔታ ያካረረው የሀገራቱ ውጥረት ኢራቃውያን ዛሬ በሺአ የሀይማኖት መሪው ሙቅታድር አል ሳድር ጥሪ አማካኝነት በዋና ከተማዋ ባግዳድ ለተቃውሞ እንዲሰባሰቡ አድርጓቸዋል፡፡
በኢራቅ የአይ ኤስ አሸባሪ ቡድንን ለመዋጋት በሚል ከ5 ሺ በላይ የአሜሪካ ወታደሮች ይገኛሉ
ምንጭ፡- ሮይተርስ