ከዋሽንግተን ፖሰቱ ጋዜጠኛ ጀማል ካሾግጂ ግድያ ጋር በተያያዘ ሳኡዲ አረቢያ ስሟ በአሉታ ሲነሳ ነበር
የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን በሳኡዲ አረቢያ የጉዞ እቅዳቸው ላይ የተነሳውን ትችት ተከላክለዋል፤ በሳኡዲ ቆይታቸው የመብት ጉዳይ አጀንዳ እንደሚሆንም ተናግረዋል።
ፕሬዝደንት ባይደን በሚቀጥለው ሳምንት በመካከለኛው ምስራቅ ጉብኝት ያደርጋሉ።
ባይደን በቆይታቸው ከሳኡዲ አረቢያው ንጉስ ሳልማን ቢን አብዱላዚዝ ጋር ውይይት ያደርጋሉ ሲል ሮይተርስ ዘግቧል።
ንጉስ ሳለማን በፈረንጆቹ 2018 ከተገደለው የዋሽንግቸን ፖስቱ ጋዜጠኛ ጀማል ካሾግጂ ግድያ አሉበት ተብሎ ይታመናል።
ዋሽንግተን ፖስት ቅዳሜ እለት ይዞት በወጣው እትም ላይ የፕሬዝዳንቱ ጉብኝት አላማ ለአሜሪካ የ80 አመት አጋር ከሆነችው ሀገር ገር ያለውን ግንኙነት ለማስተካከል መሆኑን ባይደን ጽፈዋል።
"በሳኡዲ አረቢያ የእቅድ ጉዞዮ ብዙ የማይስማሙ ይኖራሉ። በሰብአዊ መብት ላይ ያለኝ እይታ ግልጽና የቆየ ነው፤ በጉዞየም የመሠረታዊ ነጻነት ጉዳይ አጀንዳዬ ነው" ሲሉ ባይደን ጽፈዋል።
በነዳጅ ሀብቷ የምትታወቀው ሳኡዲ አረቢያ የነዳጅ ዋጋ በጨመረበት ጊዜ እንደምታስፈልግና በየመን ያለው ጦርነት እንዲቋጭ እንደማያበረታቱም ባይደን ቸናግረዋል።
አሜሪካ በመካከለኛው ምስራቅ ያለውን የኢራን ተጽእኖ እና በአለም ደረጃ ደግሞ የቻይናን ተጽእኖ መግታት ትፈልጋለች።