ብራዚል የመንግስታቱ ድርጅትና ዓለም አቀፍ ተቋማት ማሻሻያ እንዲደረግባቸው ጠየቀች
ተመድና ሌሎች ዓለም አቀፍ ተቋማት ዓለም አቀፍ ግጭቶች መከላከል አልቻሉም ስትል ተችታለች
የብራዚል ፕሬዝዳንት በፀጥታው ም/ቤት አፍሪካና ላቲን አሜሪካ ቋሚ መቀመጫ ሊኖራቸው የገባል ብለዋል
የተባበሩት መንግስታት ድርጅትና ሌሎች ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ማሻሻያሊ እንደረግባቸው ብራዚል ጠየቀች።
የብራዚል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በሪዮ ዲ ጄኔሮ መካሄድ በጀመረው የቡድን 20 አባል ሀገራት ስብሰባ ለይ ባደረጉት ንግግር ተመድ እና ዓለም አቀፍ የትብብር ተቋማት ዓለም አቀፍ ግጭቶች መከላከል አልቻሉም ሲሉ ተችተዋል።
ዓለም አቀፍ ተቋማቱ ግጭቶችን መከላከልና እና ማስቆም ባለመቻላቸው እንደገና ማሻሻያ ሊደረግባቸው ይገባል ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
የብዚል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማው ቬራ በንግግራቸው፤ የተመድ የፀጥታው ምር ቤት በጋዛ ሰርጥ እና በዩክሬን እየተካሄዱ ያሉ ጦርቶች ማስቆም አልቻለም ብለዋል።
አሁን እየተካሄዱ ካሉ ግጭቶች ጋር ተያይዞ የፀጥታው ምክር ቤት “ሽባ” ሆኗል ያሉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ፤ ሌሎች ዓለም አቀፍ ተቋማትም አሁን ያለውን ፈተና የመቋቋም አቅም የላቸውም ብለዋል።
የብራዚል ፕሬዝዳንት ሉዊዝ ኢናሲዮ ሉላ ዳ ሲልቫ ከተዘጋጁት እቅዶች ዋነኛው እንደ የተባበሩት መንግስታት፣ የአለም ንግድ ድርጅት እና ባለብዙ ወገን ባንኮች እና ሌሎች የአለምአቀፍ ተቋማት ማሻሻያ ነው።
በፕሬዝዳንት ሉላ እቅዳቸው መሰረት፤ በማደግ ላይ ያሉ ሀገራት በተመድ፣ በዓለም የንግድ ድርጅትና በሌሎች ዓለም አቀፍ ተቋማት ውስጥ ጠንካራ ውክልና እንዲኖራቸው ማድረግ ይፈልጋሉ።
ግራ ዘመሙ መሪ በአዲ አበባ በነበራቸው ቆይታ የተባበሩት መንግስታ የፀጥታው ምክር ቤትን የማስፋት ፍላጎት እንዳላቸው በድጋሚ ያነሱ