የብራዚል ፕሬዝደንት የጋዛን ጦርነት ሂትለር ከፈጸመው የዘር ማጥፋት ጋር በማነጻጸራቸው እስራኤልን አስቆጥቷል
ብራዚል በእስራኤል የሚገኙ አምባሳደሯን ወደ ሀገር ቤት መጥራቷን የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
የብራዚል ፕሬዝደንት ሉላ ዳሲልቫ የጋዛን ጦርነት ሂትለር ከፈጸመው የዘር ማጥፋት ጋር በማነጻጸራቸው እስራኤልን አስቆጥቷል።
ይህንን ተከትሎም እስራኤል የብራዚሉ ፕሬዝዳነት ሉላ ዳሲልቫ ንግግራቸውን መልሰው ካላረሙ በመካለኛዋ ምስራቅ ሀገር እንደማይፈሉ አስታውቃለለች።
የብራዚሉ ፕሬዝዳነት ሉላ ዳሲልቫ በአዲስ አበባ ባደረጉት ንግግር፤ በጋዛ እየተካሄደ ያለው ነገር በዓለም ላይ የትም አልተካሄድም፤ ከዚህ ከደም ሂተለር አይሁዶች ላይ ከፈጸመው ግድያ ውጪ ብለዋል።
- የብራዚሉ ፕሬዝደንት የጋዛውን ጦርነት ናዚ ከፈጸመው ዘርማጥፋት ጋር ማነጻጸራቸው እስራኤልን ክፉኛ አስቆጣ
- ፕሬዝደንት ሉላ በእስራኤል "የማይፈለጉ ሰው" ተብለው ተፈረጁ
በ2ኛ የዓለም ጦርነት ወቅት የጀርመኑ መሪ ሂትለር ከ6 ሚሊየን በላይ አይሁዳዉያንን መጨፍጨፉ የሚነገር ሲሆን፤ የብራዚሉ ፕሬዝዳንት የጋዛውን ጦርንት ከናዚ ሆሎካስት ጋር ማመሳሰላቸው ነው እስራኤልን ያስቆጣው።
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በጉዳዩ ላይ በሰጠቱት አስተያየት፤ “የፕሬዝዳንት ሉላ ንግግር ክብርን ዝቅ የሚያደርግ እና አሳዛኝ ነው” ብለዋል።
በትናንትናው እለት የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢስራኤል ካትዝ፤ ፕሬዝዳንት ሉላ ንግግራቸውን መልሰው እስኪያርሙ ድረስ በሀገሪቱ ተቀባይነት እንደሌላቸው አስታውቀዋል።
ካትዝ በእስራኤል ለሚገኙት የብራዚል አምባሳደር በሰጡት መግለጫ፤ “የፕሬዝዳንቱ ንግግር መቼም የማይረሳ እና ይቅር የማይባል ነው፤ በራሴ ስም እና በእስራኤል ህዝብ ስም ፕሬዝዳንት ሉላ ንግግራቸውን እስካልስተካከሉ ድረስ በሀገሪቱ ተቀባይነት እንደሌላነች ንገራቸው” ብለዋል።
ለዚህ ምለሽም ብራዚል በሀገሯ የሚገኙትን የእስራኤል አምባሳደር ዳኒኤል ዞንሸይንን ለማናገር መጥራቷን አስታውቃዋለች።
በተጨማሪም የብራዚል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በእስራኤል የሚገኙትን አምባሳደር ፍሬድሪኮ ሜየርን ለምክክር ወደ ሀገር ቤት መጥራቱንም አስታውቋል።