በነገው እለት ማንቸስተር ዩናይትድ የጀርመኑን ባየር ሙኒክ የሚገጥምበት ጨዋታ ተጠባቂ ነው
የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የ2023/24 ውድድር ዛሬ በሚደረጉ ጨዋታዎች ጅማሮውን ያገኛል።
በምድብ ስድስት ኤሲ ሚላን በሳንሲሮ ኒውካስትልን የሚያስተናግድበት ጨዋታ ይጠበቃል።
ከ20 አመት በኋላ ወደ ሻምፒዮንስ ሊጉ የተመለሰው ኒውካስትል እና ኤሲ ሚላን ጨዋታ ምሽት 1 ስአት ከ45 ላይ ይደረጋል።
ከዚሁ ምድብ የፈረንሳዩ ፓሪስ ሴንት ጄርሜን የጀርመኑን ዶርትሙንድ ምሽት 4 ስአት ላይ ያስተናግዳል።
የአምናው ሻምፒዮን ማንቸስተር ሲቲም በኢትሃድ የሰርቢያውን ሬድ ስታር ቤልግሬድ ይገጥማል።
አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ “ሁሌም ሻምፒዮን ለመሆን የመጀመሪያውን ጨዋታ ለማሸነፍ ትኩረት እንሰጣለን” የሚል አስተያየት ሰጥተዋል።
ሲቲ በምሽቱ ጨዋታ ጆን ስቶንስ፣ ጃክ ግሪሊሽ፣ ማቲዮ ኮቫቺች እና ኬቪን ደ ብሩይነን በጉዳት ምክንያት አያሰልፍም።
በሌላኛው የምድብ 7 ጨዋታ የስዊዘርላንዱ ክለብ ያንግ ቦይስ ከጀርመኑ አርቢ ላይፕዚሽ ጋር ምሽት 1 ስአት ከ45 ላይ ይጫወታል።
በምድብ ስምንት የተደለደለው ባርሴሎናም ምሽት 4 ስአት ላይ ከቤልጂየሙ አንትዌርፕ ክለብ ጋር ጨዋታውን ያደርጋል።
በነገው እለት ከሚጠበቁት ጨዋታዎች መካከል ማንቸስተር ዩናይትድ ከሜዳው ውጭ ባየር ሙኒክን የሚገጥምበት ጨዋታ አንዱ ነው።
አርሰናልም በኤምሬትስ የሆላንዱን ፒኤስቪ የሚያስተናግድበት ጨዋታ ተጠባቂ ነው።
መድፈኞቹ እና ቀያዮቹ ሰይጣኖች የመጀመሪያ የሻምፒዮንስ ሊግ የምድብ ጨዋታቸውን የሚያደርጉት በተመሳሳይ ምሽት 4 ስአት ላይ ነው።