የ2023/24 የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ድልድል ይፋ ሆነ
የእንግሊዝ ክለቦች ከኒውካስትል ዩናይትድ ውጪ ያሉት በአንጻራዊነት ቀለል ባለ ምድብ ውስጥ ተደልድለዋል
ፒኤስጂ፣ ቦርስያ ዶርትመንድ፣ እና ኤሲ ሚላንና ኒውካስትል ዩናይትድ በምድ ስድስት ተገናኝተዋል
የ2023/24 የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ድልድል ተካሄደ።
ተወዳጁ የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ የ2023/24 የውድድር መርሀ ግብር በፈረንሳይ ሞናኮ ይፋ ተደርጓል።
በውድድሩ አራት ክለቦችን ከሳተፈው የእንግሊዝ ክለቦች ውስጥ ኒውካስትል ዩናይትድ በምድብ ስድስት ከፒኤስጂ፣ ቦርሲያ ዶርትሙንድ እና ኤሲ ሚላን ጋር ተደልድሏል።
በምድብ አንድ የጀርመኑ ባየር ሙኒክ ፣ማንችስተር ዩናይትድ ፣ኮፐንሀገን እና የቱርኩ ጋላታሳራይ ተደልድለዋል።
- ለአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ያለፉ የአውሮፓ ክለቦች እነማን ናቸው?
- የአውሮፓ ተጫዋቾች ዝውውር አዳዲስ መረጃዎች
በምድብ ሁለት ደግሞ ሲቪያ፣ አርሰናል፣ ፒኤስቪ እንዲሁም ሌንስ ሲደለደሉ የጣልያኑ ሻምፒዮን ናፖሊ ፣ሪያል ማድሪድ፣ ብራጋ እና ዩኒየን በርሊን ደግሞ በምድብ ሶስት የተደለደሉ ክለቦች ናቸው።
በምድብ አራት፣ቤኔፊካ፣ የአምናው የቻምፒዮንስ ሊግ የፍጻሜ ተፋላሚ ኢንተር ሚላን፣ ሳልዝበርግ እና ሪያል ሶሴዳድ ሲደለደሉ፣ ፊኖርዶ፣ አትሌቲኮ ማድሪድ፣ ላዚዮ እና ሴልቲክ በምድብ አምስት ላይ ተቀምጠዋል።
የአምናው ቻምፒዮንስ ሊግ ውልንጫ አሸናፊው ማንችስተር ሲቲ፣ ሌፕዚግ፣ ክሬቭና ዝቬዝዳ እና ያንግ ቦይስ በምድብ ሰባት ተደልድለዋል።
በመጨረሻው ምድብ ስምንት ደግሞ ባርሴሎና ፣ፖርቶ፣ ሻካታር ዶኔስክ እና ሮያል አንትዌርፕ መደልደላቸውን የውድድሩ ባለቤት የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ በድረገጹ አስታውቋል።
የ2023/24 ዓመት የቻምፒዮንስ ሊግ ውድድር መስከረም 8 ቀን 2016 ዓ. ም የሚጀመር ሲሆን የፍጻሜው ጨዋታ በእንግሊዝ ለንደን ዊምብሌይ ስታዲያም ይካሄዳል ተብሏል።