ከ800 ሺህ ዶላር ካሽ ጋር የተያዙት ቻይናዊን የወርቅ ነጋዴዎች
ቻይናዊያኑ ከህገ ወጥ ማዕድን አውጪዎች የገዙት ከፍተኛ መጠን ያለው ወርቅም በጸጥታ ሀይሎች ተይዞባቸዋል
ገንዘቡ እና ወርቁ በመኪና ውስጥ ተሸሽጎ ተይዟል
ከ800 ሺህ ዶላር ጋር የተያዙት ቻይናዊን የወርቅ ነጋዴዎች
ምዕራብ አፍሪካዊቷ ዲሞክራቲክ ኮንጎ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎቿ በአስከፊ ድህነት ውስጥ እንደሚኖሩ የተመድ ሪፖርት ያስረዳል፡፡
በአንጻሩ ግን ሀገሪቱ አልማዝ እና ወርቅን ጨምሮ በዓለም ገበያ እጅግ ተፈላጊ የሆኑ አያሌ ማዕድናት ባለቤት ናት፡፡
በዲሞክራቲክ ኮንጎ በመቶዎች የሚቆጠሩ ታጣቂዎች መንቀሳቀሳቸው እና የሀገሪቱ ፌደራል መንግስት አቅም መዳከም ማዕድናቱን መቆጣጠር እንዳይችል አድርጎታል፡፡
የተለያዩ ሀገራት ዜጎችም ይህን ማዕድን በርካሽ ለመግዛት በሚል ከታጣቂዎቹ ጋር ጥብቅ ቁርኝት በመፍጠር የሕገ ወጥ ማዕድን ግብይቱ መድራቱን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
የዲሞክራቲክ ኮንጎ የጸጥታ ሀይሎች ከአማጺያን ከፍተኛ መጠን ያለው ወርቅ ገዝተው በማጓጓዝ ላይ የነበሩ ቻይናዊንን መያዛቸውን ገልጸዋል፡፡
ቻይናዊያኑ የተያዙት ከ800 ሺህ ዶላር ካሽ እና ከበርካታ ጥፍጥፍ ወርቅ ጋር እንደሆነም በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡
በደቡባዊ ኪቩ ግዛት የተያዙት እነዚህ ቻይናዊያን ማዕድናትን ከአማጺያን ሲገዙ የነበሩ ናቸው ተብሏል፡፡
በቅርቡ 17 ቻይናዊያን በተመሳሳይ ወርቅ ከአማጺያን ሲገዙ በሀገሪቱ የጸጥታ ሀይሎች ከተያዙ በኋላ በድርድር እንዲለቀቁ መደረጉ በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡
ቻይና 83 ቢሊዮን ዶላር ዋጋ ያለው የወርቅ ክምችት አገኘች
ዲሞክራቲክ ኮንጎ በቅርቡ የአሜሪካው አፕል ኩባንያ ማዕድናትን ከአማጺያን እየገዛ ነው የሚል ክስ አቅርባ ነበር፡፡ ኩባንያው ክሱን ውድቅ ያደረገ ቢሆንም የማዕድናት ግብይት ሰንሰለቱን ይፋ እንዲያደርግ ጥያቄም ቀርቦለታል፡፡
ሌላኛው የዲሞክራቲክ ኮንጎ ጎረቤት የሆነችው ሩዋንዳ አማጺያንን በማስታጠቅ እና የሕገ ወጥ ማዕድን ግብይት ሰንሰለት ውስጥ እጇ አለበት የሚል ክስም ቀርቦባታል፡፡
ይሁንና የሩዋንዳ መንግስት ከዲሞክራቲክ ኮንጎ የሚቀርብበትን ክስ እንደማይቀበል እና ጉዳዩ የዲአርሲ የውስጥ ጉዳይ ነው በሚል ውድቅ አድርጓል፡፡