ኢኮኖሚ
በብሔራዊ ባንክ ተመን የአንድ ግራም ወርቅ ዋጋ ስንት ደረሰ?
ባንኩ ባለ 24 ካራት 1 ግራም ወርቅ 80.5932 ዶላር (8 ሺህ 750 ብር) እየገዛ ነው
ብሔራዊ ባንክ ወርቅ የሚገዛው በዓለም አቀፍ እለታዊ ዋጋ መሆኑን ማሳወቁ ይታወሳል
ኢትዮጵያ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ስርአት መከተል ከጀመረች በኋላ ብሔራዊ ባንክ ወርቅ የሚገዛው በአለምአቀፍ እለታዊ ዋጋ መሆኑን መግለጹ ይታወቃል።
በዚህም ባንኩ እለታዊ የወርቅ መግዣ ዋጋ በድረ ገጹ ይፋ እያደረገ ይገኛል።
ብሄራዊ ባንክ የዛሬ የነሃሴ 15 2016 የወርቅ መግዣ ዋጋን ይፋ ሲያደርግ ባለ 24 ካራት 1 ግራም ወርቅ 80.5932 የአሜሪካ ዶላር ወይም በእለቱ የብሄራዊ ባንክ የምንዛሬ ዋጋ 8 ሺህ 750 ብር እየገዛ መሆኑ ተመላክቷል።
ባለ 23 ካራት 1 ግራም ወርቅ 77.2352 የአሜሪካ ዶላር ወይም በእለቱ የብሄራዊ ባንክ የምንዛሬ ዋጋ 8 ሺህ 385 ብር እየገዛ መሆኑንም ነው ያስታወቀው።
ባለ 22 ካራት 1 ግራም ወርቅ ደግሞ በ73.8771 ዶላር (8 ሺህ 21 ብር) እየገዛ ይገኛል።
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ያወጣውን እለታዊ የወርቅ መግዣ ዋጋ በቀጣዩ ሰንጠረዥ ይመልከቱ፦