በስብሰባው "የተለየ ውጤት ሊኖር እንደሚችል" የኮፕ 28 ፕሬዝደንት ተናገሩ
ጃበር "ተስፋ አደርጋለሁ፣ አቅሙ እስካለን ድረስ ያልተጠበቁ ውጤቶችን ማምጣት እንችላለን" ብለዋል
ዶክተር ጃብር ስብሰባው የአለም የሙቀት መጠን 1.5 ዲግሪ ሴልሺየስ ሆኖ እንዲቆይ የሚያደርግ ውጤት ይኖረዋል ሲሉ ተናግረዋል
በስብሰባው "የተለየ ውጤት ሊኖር እንደሚችል" የኮፕ 28 ፕሬዝደንት ተናገሩ
በአረብ ኢምሬትስ በሚካሄደው የአየር ንብረት ስብሰባ "የተለየ ውጤት ሊኖር እንደሚችል" የኮፕ28 ስብሰባ ፕሬዝደንት ዶክተር ሱልጣን ቢን መሀመድ አል ጃብር ለዘጋርዲያን ጋዜጣ ተናግረዋል።
ዘጋርዲያን ፕሬዝደንቱን ጠቅሶ እንደዘገበው የአለም የሙቀት መጠን ከ1.5 ዲግሪ ሴልሺየስ እንዳይበልጥ ለማድረግ ስምምነት እንደሚኖር ተናግረዋል።
የአረብ ኢምሬትስ የኢንዱስትሪ እና አድቫንስድ ቴክኖሎጂ ሚኒስትር እንዲሁም የኮፕ28 ሰብሰባ ፕሬዝደንት የሆኑት ዶክተር ጃብር ስብሰባው የአለም የሙቀት መጠን 1.5 ዲግሪ ሴልሺየስ ሆኖ እንዲቆይ የሚያደርግ ውጤት ይኖረዋል ሲሉ ተናግረዋል።
ዶክተር ጃብር ከእንግሊዙ ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ባለፉት ሳምንት በኮፕ28 ስብሰባ ስምምነት ይደረግባቸዋል ተብለው የሚጠበቁት ጉዳዮች በጥሩ ሂደት ላይ ናቸው።
አረብ ኢምሬትስን በመወከል ስብሰባውን የሚመሩት ዶክተር ጃብር አለም የበካይ ጋዝ ልቀትን በ2030 ሳይንስ ወደሚፈቅደው ደረጃ ለማድረስ በሚያስችል እቅድ ላይ ሊስማማ እንደሚችልም ተናግረዋል።
ጃበር "ተስፋ አደርጋለሁ፣ አቅሙ እስካለን ድረስ ያልተጠበቁ ውጤቶችን ማምጣት እንችላለን" ብለዋል።
እሰከ 2030 የአለም የሙቀት መጠንን 1.5 ዲግሪ ሴልሺየስ ሆኖ እንዲቆይ የሚያስችል እቅድ መተግበር የስብባው ግብ መሆኑን ዶክተር ጀብር ተናግረዋል።
በአረብ ኢምሬትስ ለሁለት ሳምንታት በሚካሄደው ጉባኤ ፕሬዝደንቶች እና ጠቅላይ ሚኒስትሮች እንዲሁም የተለያዩ አለምአቀፍ ተቋማት ይሳተፋሉ።
በስብሰባው ከ70ሺ በላይ ልዑካን ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል። ከ198 ሀገራት የተውጣጡ ሚኒስትሮች እና ከፍተኛ ባለስልጣናት የሙቀት አማቂ ጋዞች ልቀትን በአስቸኳይ መቀነስ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ይወያያሉ።
ዶ/ር ጃብር አል ጃበር በሳዑዲ አረቢያ ያደረጉትን ንግግር በመጥቀስ በተለይ መንግስት “በጣም ትልቅ ተስፋ ያላቸውን የአየር ንብረት እርምጃዎች ውጤት ለማምጣት እንዲሰራ ያቀረብኩትን ጥሪ ተቀባይነት ካገኘ በኋላ አዲስ ቃል መግባት ይቻላል" ብለዋል።