የፖሪስ የአየር ንብረት ጉባኤ ስኬቶች ምንድናቸው?
የፖሪስ የአየር ንብረት ጉባኤ የተካሄደው በፈረንጆቹ 2015 ነበር
ጉባኤው 200 ሀገራት ተሰባስበው የአየር ንብረትን ለመዋጋት የጋራ ግብ እንዲያስቀምጡ አድርጓቸዋል
የፖሪስ የአየር ንብረት ጉባኤ ስኬቶች ምንድናቸው?
የፖሪስ የአየር ንብረት ጉባኤ የተካሄደው በፈረንጆቹ 2015 ነበር።
በጉባኤው በርካታ ስኬቶች ተመዝግበዋል። አለምአቀፍ ስምምነት፦ ጉባኤው 200 ሀገራት ተሰባስበው የአየር ንብረትን ለመዋጋት የጋራ ግብ እንዲያስቀምጡ አድርጓቸዋል። በጉባኤው የአለምን የሙቀት መጠን ከ2 ዲግሪ ሼልሺየስ በታች ለማድረስ ግብ ተቀምጧል።
ናሺናሊ ዲተርምንድ ኮንትሪቡሽን(ብሔራዊ መዋጭ) ፦
እያንዳንዱ ተሳታፊ ሀገር የበካይ ጋዝ ልቀትን እና የአየር ንብረት ለውጥን ለመቀነስ የሚያስችላቸውን እቅድ አዘጋጅተዋል። ይህም የአየር ንብረት ለውጥን ለመዋጋት በሚደረገው ጥረት የአደጉ ሀገራት ብቻ ሳይሆኑ ሁሉም እንዲሳፉ አድርጓቸዋል።
ግልጸኝን እና ተጠያቂት፦
ስምምነቱ ሀገራት የአየር ንብረት ለውጥ ግባቸውን ምን ያህል አሳክተዋል የሚል የክትትል እና የሪፖርት ማዕቀፍ እንዲዘጋጅ አስችሏል። ግልኝነቱ ሀገራቱ ላወጡት እቅድ ቁርጠኛ እንዲሆኑ ለማድረግ ወሳኝ ነው።
የፋይናንስ ኮሚትመንት፦
የፖሪሱ ስምምነት የአደጉ ሀገራት፣ በማድግ ላይ ያሉ ሀገራት ለሚያደርጉት የአየር ንብረት ለውጥ ቅነሳ ጥረት የፋይናንስ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ይጠቅሳል። በማደግ ላይ ያሉ ሀገራትን ለመርዳት በ2020 100ቢሊዮን ዶላር ለማውጣት እቅድ ተይዞ ነበር።
የረጅም ጊዜ ግብ፦
ስምምነቱ በምዕተ አመቱ ሁለተኛ አጋማሽ ላይ የአየር ብክለትን ወደ 'ኔት ዜሮ' ለማድረስ እንደሚያስፈልግም ይገልጻል። ይህ የሚሆነው የሚለቀቀው የበካይ ጋዝ መጠን ከከባቢ አየር ከሚወገደው ጋር እኩል ሲሆን ነው።
የፖሪሱ ስምምነት በአየር ንብረት ለውጥ ዙሪያ የተደረገ ትልቅ ስብሰባ ቢሆንም፣በአተገባበሩ ላይ ውይይቶች እየተካሄዱ ናቸው። ሀገራትም የአየር ንብረት ለውጥን ለመቀነስ ያቀረቡትን እቅድ እየከለሱ ይገኛሉ።