የኮፕ28 ጉባኤ ከህዳር 20 እስከ ታህሳስ 1 ድረስ በዱባይ እንደሚካሄድ ይጠበቃል
የኮፕ28 አየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ አበይት ክስተቶች ምን ምን ናቸው?
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በየዓመቱ በአየር ንብረት ለውጥ ዙሪያ የዓለም ሀገራት፣ የአየር ንብረት ለውጥ ባለሙያዎችን እና ሌሎች የሚመለከታቸውን አካላት ጋር ይመክራል፡፡
ይህ ጉባኤ በተመድ አባል ሀገራት እየተዟዟረ በየዓመቱ የሚካሄድ ሲሆን የዘንድሮው ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ በተባበሩት አረብ ኢምሬት አስተናጋጅነት ይካሄዳል፡፡
በዱባይ በሚካሄደው በዚህ ጉባኤ ዋና ዋና ክስተቶች ምን ምን ሊሆኑ እንደሚችል አስቀድሞ ለተሳታፊዎች ይፋ ተደርጓል፡፡
የመጀመሪያ ክስተት የጤና የጤና ቀን የሚባል ሁነት የተዘጋጀ ሲሆን የዓለም ሀገራት የጤና ጥበቃ ሚኒስትሮች እንደሚሳተፉበት ተገልጿል፡፡
ሚኒስትሮቹ የአየር ንብረት ለውጥ በጤና ላይ ስለሚያደርሳቸው ጉዳቶች ዙሪያ ተወያይተው የውሳኔ ሀሳብ ይቀርባሉ ተብሏል፡፡
የአየር ንብረት ለውጥ ጭንቀት ሊያስከትል ይችላል?
ሌላኛው በዚህ ጉባኤ ላይ የሚካሄደው አበይት ክስተት በምግብ ስርዓት እና ግብርና ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት የሚደረግበት ሲሆን በተለይም የአየር ንብረት ለውጥ በምግብ ዋስትና ላይ እያደረሰው ስላለው ጉዳት ውይይት እንደሚደረግ ይጠበቃል፡፡
ዓለም አቀፍ ንግድ ቀን የሚባለው ሶስተኛው የኮፕ28 አበይት ክስተት አካል ሲሆን የዓለም በካይ ጋዝ ልቀት፣ የታዳሽ ሀይል ሽግግር እና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር ይደረግበታል፡፡
አራተኛው አበይት ክስተት ደግሞ የሀይማኖት መሪዎች የሚሳተፉበት እና የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል የጋራ ሀላፊነት በሚወሰድበት ሁኔታ እንደሚወያዩ ይጠበቃል ተብሏል፡፡
ሌላኛው የጉባኤው አበይት ክስተት በዓለም የመጥፋት አደጋ የተደቀነባቸው ህዝቦች በአየር ንብረት ለውጥ ዙሪያ የሚመክሩበት ክስተት ሲሆን በተመድ የዓየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ከዓለም ህዝብ ፊት ቀርበው ውይይት እንደሚያደርጉ ይጠበቃል፡፡