ቻይና የኮሮና ቫይረስን ለመቆጣጠር ከተሞችን መዝጋቷን ቀጥላለች፡፡
በቫይረሱ የሟቾች ቁጥር እየጨመረ መሆኑን ተከትሎ ቻይና በሽታውን ለመቆጣጠር በሁቤይ ግዛቷ እና አካባቢው የሚገኙ ከተሞችን ዘግታለች፡፡ በማእከላዊ ቻይና 20 ሚሊዮን ያክል ህዝብ የሚኖርባቸው ወደ 10 ከተሞች የጉዞ ማዕቀብ ተጥሎባቸዋል፡፡ ባጠቃላይ ስጋት ባለባቸው አካባቢዎች 30 ሚሊዮን ዜጎቿ ከቀዬያቸው እንዳይንቀሳቀሱ አግዳለች፡፡ በቻይና ከሁቤይ ግዛት ውጭ ለመጀመሪያ ጊዜ 2 ሰዎች በቫይረሱ ሞተዋል፡፡ በዉሀን ከተማ የኮሮና ቫይረስ ብቻ ታማሚዎች የሚታከሙበት በ6 ቀናት ይጠናቀቃል የተባለ 1,000 አልጋዎች ያሉት ሆስፒታል እየተገነባ ነው፡፡